ሐዋርያት ሥራ 20:4-38

ሐዋርያት ሥራ 20:4-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሱሲጴጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ እንዲሁም ጢሞቴዎስ ዐብረውት ሄዱ። እነዚህም ሰዎች ወደ ፊት ቀድመውን በጢሮአዳ ጠበቁን። እኛ ግን የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሣን፤ ከዐምስት ቀንም በኋላ ከሌሎቹ ጋራ በጢሮአዳ ተገናኘን፤ በዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን። በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቍረስ ተሰብስበን ሳለን፣ ጳውሎስ በማግስቱም ለመሄድ ስላሰበ፣ ከእነርሱ ጋራ ይነጋገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አራዘመ። በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራት ነበር። አውጤኪስ የተባለ አንድ ጐበዝም በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ እንቅልፍ እንቅልፍ አለውና ጭልጥ ብሎ ተኛ፤ ከሦስተኛውም ፎቅ ቍልቍል ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ተጋድሞ ዐቀፈውና፣ “ሕይወቱ በውስጡ ስላለች ሁከት አትፍጠሩ!” አላቸው። ተመልሶም እንደ ገና ወደ ፎቁ ወጣ፤ እንጀራውንም ቈርሶ በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ብዙ ከተናገረ በኋላ ተነሥቶ ሄደ። ሰዎችም ያን ጐበዝ ሕያው ሆኖ ወሰዱት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ። እኛ ግን ጳውሎስን ለመቀበል ቀድመን ወደ መርከቡ ሄድን፤ ከዚያም በመርከብ ወደ አሶን ተጓዝን፤ ይህን ያደረግነውም ጳውሎስ በየብስ በእግሩ ሊሄድ ስላሰበ ነበር። በአሶን ከተገናኘንም በኋላ፣ ተቀብለነው ዐብረን በመርከብ ወደ ሚጢሊኒ ሄድን። በማግስቱም በመርከብ ተጕዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን። ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ ዐምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ። በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ አውራጃ ከገባሁባት ከመጀመሪያዋ ዕለት አንሥቶ ዘወትር ከእናንተ ጋራ እንዴት እንደ ኖርሁ ታውቃላችሁ። ምንም እንኳ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ መከራ ቢያደርሱብኝም፣ ጌታን በታላቅ ትሕትናና በእንባ ከማገልገል አልተቈጠብሁም፤ በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም። በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ። “አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው። ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት። “አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ። ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚህች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና። ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ። እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሠርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ። ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ። ስለዚህ ተጠንቀቁ! ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ምን ያህል ሳላቋርጥ በእንባ እያንዳንዳችሁን እንደ መከርኋችሁ አስታውሱ። “አሁንም ለእግዚአብሔር፣ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ። የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋራ ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። በጕልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ምስጉን ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።” ይህን ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋራ ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም ዐንገቱን ዐቅፈው ሳሙት። ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:4-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከእ​ር​ሱም ጋር የቤ​ርያ ሀገር ሰው የሚ​ሆን ሱሲ​ጳ​ጥ​ሮስ፥ የተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሰዎች አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስና ሲኮ​ን​ዱስ፥ የደ​ር​ቤኑ ሰው ጋይ​ዮ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ የእ​ስያ ሰዎች የሚ​ሆኑ ቲኪ​ቆ​ስና ጥሮ​ፊ​ሞ​ስም አብ​ረ​ውት ሄዱ። እነ​ር​ሱም ቀድ​መ​ውን ሄደው በጢ​ሮ​አስ ቆዩን። እኛ ግን ከፋ​ሲካ በኋላ ከፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተነ​ሥ​ተን በባ​ሕር ላይ ተጕ​ዘን በአ​ም​ስት ቀን ወደ ጢሮ​አስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን። ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመ​ባ​ረክ ተሰ​ብ​ስ​በን ሳለን ጳው​ሎስ በማ​ግ​ሥቱ የሚ​ሄድ ነውና ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመረ፤ እስከ መን​ፈቀ ሌሊ​ትም ድረስ ትም​ህ​ር​ቱን አስ​ረ​ዘመ። ተሰ​ብ​ስ​በን በነ​በ​ር​ን​በት ሰገ​ነ​ትም ብዙ መብ​ራት ነበር። ስሙ አው​ጤ​ክስ የሚ​ባል አንድ ጐል​ማሳ ልጅም በመ​ስ​ኮት በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ ከባድ እን​ቅ​ልፍ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም ትም​ህ​ር​ቱን ባስ​ረ​ዘመ ጊዜ ያ ጐል​ማሳ ከእ​ን​ቅ​ልፉ ብዛት የተ​ነሣ ከተ​ኛ​በት ከሦ​ስ​ተ​ኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳ​ው​ንም አነ​ሡት። ጳው​ሎ​ስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅ​ፎም ያዘው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ “ነፍሱ አለ​ችና አት​ደ​ን​ግጡ” አላ​ቸው። ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሰገ​ነት ወጣ፤ ማዕ​ዱ​ንም ባርኮ በላ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብዙ ትም​ህ​ርት አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚያ በኋ​ላም ተነ​ሥቶ ሄደ። ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ደኅና ሆኖ ወሰ​ዱት፤ እጅ​ግም ደስ አላ​ቸው። እኛ ግን በመ​ር​ከብ ሆነን ወደ አሶስ ሄድን፤ ከዚያ ጳው​ሎ​ስን ልን​ቀ​በ​ለው እንሻ ነበ​ርና፤ እን​ደ​ዚሁ በእ​ግር እን​ደ​ሚ​መጣ ነግ​ሮን ነበ​ርና ተቀ​በ​ል​ነው። አሶ​ስም ደረ​ስን፤ በመ​ር​ከ​ብም ይዘ​ነው ወደ ሚጢ​ሊኒ ሄድን። በማ​ግ​ሥ​ቱም ከዚያ ወጥ​ተን በኪ​ዮስ ፊት ለፊት ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሳሞስ አለ​ፍን፤ በት​ሮ​ጊ​ሊ​ዮም ተቀ​መ​ጥን፤ ከዚህ ቀን በኋ​ላም ወደ መሊጡ ደረ​ስን። ጳው​ሎ​ስም በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ በኤ​ፌ​ሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚ​ቻ​ለ​ውም ቢሆን ለበ​ዓለ ኀምሳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ድ​ረስ ቸኵሎ ነበ​ርና። ከመ​ሊ​ጡም የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ቀሳ​ው​ስት ይጠ​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ኤፌ​ሶን ላከ። ወደ እር​ሱም በመጡ ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወደ እስያ ከገ​ባ​ሁ​በት ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ጀምሮ በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ና​ንተ ዘንድ እንደ ተቀ​መ​ጥሁ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ገ​ለ​ገ​ልሁ በፍ​ጹም መከ​ራና በል​ቅሶ ከአ​ይ​ሁ​ድም ሴራ የተ​ነሣ በደ​ረ​ሰ​ብኝ ፈተና እየ​ተ​ጋ​ደ​ልሁ፥ በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤ አሁ​ንም እነሆ በመ​ን​ፈስ ታሥሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን በዚያ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝን አላ​ው​ቅም። ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ፦ በየ​ከ​ተ​ማው መከ​ራና እስ​ራት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል ብሎ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል። ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ወን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ሩጫ​ዬን እን​ድ​ጨ​ር​ስና መል​እ​ክ​ቴ​ንም እን​ድ​ፈ​ጽም ነው እንጂ ለሰ​ው​ነቴ ምንም አላ​ስ​ብ​ላ​ትም። አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ። እኔ ከሁ​ላ​ች​ሁም ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ እነሆ ዛሬ በዚች ሌሊት እመ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ኋ​ለሁ። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም። አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ። ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ። ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ። ስለ​ዚ​ህም ትጉ፤ እኔ ሁላ​ች​ሁ​ንም ሳስ​ተ​ምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እን​ባዬ እን​ዳ​ል​ተ​ገታ ዐስቡ። አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ሊያ​ን​ጻ​ችሁ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም ሁሉ መካ​ከል ርስ​ትን ሊሰ​ጣ​ችሁ ለሚ​ች​ለው ለጸ​ጋው ቃል አደራ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ። ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። እነ​ዚ​ህም እጆች ለም​ሻው ነገ​ርና ከእ​ኔም ጋር ላሉት እን​ዳ​ገ​ለ​ገሉ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።” ይህ​ንም ከአለ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ አብ​ረ​ውት ካሉት ሁሉ ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት። ይል​ቁ​ንም “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን አታ​ዩ​ትም” ስለ አላ​ቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መር​ከ​ብም ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:4-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሱሲጴጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ እንዲሁም ጢሞቴዎስ ዐብረውት ሄዱ። እነዚህም ሰዎች ወደ ፊት ቀድመውን በጢሮአዳ ጠበቁን። እኛ ግን የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሣን፤ ከዐምስት ቀንም በኋላ ከሌሎቹ ጋራ በጢሮአዳ ተገናኘን፤ በዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን። በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቍረስ ተሰብስበን ሳለን፣ ጳውሎስ በማግስቱም ለመሄድ ስላሰበ፣ ከእነርሱ ጋራ ይነጋገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አራዘመ። በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራት ነበር። አውጤኪስ የተባለ አንድ ጐበዝም በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ እንቅልፍ እንቅልፍ አለውና ጭልጥ ብሎ ተኛ፤ ከሦስተኛውም ፎቅ ቍልቍል ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ተጋድሞ ዐቀፈውና፣ “ሕይወቱ በውስጡ ስላለች ሁከት አትፍጠሩ!” አላቸው። ተመልሶም እንደ ገና ወደ ፎቁ ወጣ፤ እንጀራውንም ቈርሶ በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ብዙ ከተናገረ በኋላ ተነሥቶ ሄደ። ሰዎችም ያን ጐበዝ ሕያው ሆኖ ወሰዱት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ። እኛ ግን ጳውሎስን ለመቀበል ቀድመን ወደ መርከቡ ሄድን፤ ከዚያም በመርከብ ወደ አሶን ተጓዝን፤ ይህን ያደረግነውም ጳውሎስ በየብስ በእግሩ ሊሄድ ስላሰበ ነበር። በአሶን ከተገናኘንም በኋላ፣ ተቀብለነው ዐብረን በመርከብ ወደ ሚጢሊኒ ሄድን። በማግስቱም በመርከብ ተጕዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን። ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ ዐምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ። በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ አውራጃ ከገባሁባት ከመጀመሪያዋ ዕለት አንሥቶ ዘወትር ከእናንተ ጋራ እንዴት እንደ ኖርሁ ታውቃላችሁ። ምንም እንኳ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ መከራ ቢያደርሱብኝም፣ ጌታን በታላቅ ትሕትናና በእንባ ከማገልገል አልተቈጠብሁም፤ በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም። በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ። “አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው። ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት። “አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ። ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚህች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና። ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ። እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሠርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ። ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ። ስለዚህ ተጠንቀቁ! ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ምን ያህል ሳላቋርጥ በእንባ እያንዳንዳችሁን እንደ መከርኋችሁ አስታውሱ። “አሁንም ለእግዚአብሔር፣ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ። የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋራ ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። በጕልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ምስጉን ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።” ይህን ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋራ ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም ዐንገቱን ዐቅፈው ሳሙት። ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:4-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤ እነዚህም ወደ ፊታችን አልፈው በጢሮአዳ ቆዩን። እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን። ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፥ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ። ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም፦ ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው። ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ። ብላቴናውንም ደኅና ሆኖ ወሰዱት እጅግም ተጽናኑ። እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና። በአሶንም ባገኘን ጊዜ ተቀብለነው ወደ ሚጢሊኒ መጣን፤ በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፥ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤ ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሴራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም። አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፥ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደ ሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ፦ እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል። ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ። ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ። ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤ ይልቁንም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:4-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ። እነርሱ ቀድመውን ሄደው በጢሮአዳ ቈዩን። እኛ ግን ከቂጣ በዓል በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተሳፍረን በአምስት ቀን እነርሱ ወዳሉበት ወደ ጢሮአዳ ደረስንና እዚያ ሰባት ቀን አሳለፍን። ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ቈርሶ በአንድነት ለመብላት ተሰበሰብን፤ ጳውሎስ በማግስቱ መሄድ ስለ ነበረበት ለተሰበሰቡት ሰዎች ይናገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት አስረዘመ። እኛ በተሰበሰብንበት ፎቅ ብዙ መብራት ነበር። ኤውጤኪስ የተባለ አንድ ወጣት በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን በማስረዘሙ ወጣቱ ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስላሸነፈውም ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሰዎች ባነሡት ጊዜ ሞቶ አገኙት። ነገር ግን ጳውሎስ ወርዶ በልጁ ላይ ጐንበስ በማለት አቀፈውና “ገና በሕይወት አለ፤ አትደንግጡ!” አለ። ጳውሎስ ወደ ፎቅ ተመልሶ ወጣና እንጀራ ቈርሶ ከአማኞች ጋር በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ከቈየ በኋላ ሄደ። ሰዎቹም የዳነውን ወጣት ወደ ቤት ወሰዱት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ። ጳውሎስን ለማሳፈር ስለ አሰብን እኛ ቀድመን በመርከብ ወደ አሶስ ሄድን፤ ይህንንም ያደረግነው ጳውሎስ እስከ አሶስ ድረስ በእግሩ ለመሄድ ስለ ወሰነና እንዲህ እንድናደርግ ስለ አዘዘን ነው። ከእርሱ ጋር በአሶስ በተገናኘን ጊዜ በመርከብ አሳፍረነው ወደ ሚጢሊኒ አብረን ሄድን። በማግስቱ ከዚያ ተነሥተን በኪዮስ ፊት ለፊት ወዳለው ስፍራ በመርከብ ደረስን፤ በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞስ ተሻገርንና በማግስቱ ወደ ሚሊጢ ደረስን። ጳውሎስ በእስያ ጊዜ እንዳያባክን ብሎ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ፈለገ፤ ይህንንም ያደረገው ለጰንጠቆስጤ በዓል በኢየሩሳሌም ለመገኘት አስቦ ስለ ነበር ነው። ጳውሎስ ከሚሊጢ ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን አስጠራ፤ ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እስያ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤ በአይሁድ ሤራ ምክንያት መከራ ቢደርስብኝም እንኳ በፍጹም ትሕትናና በእንባ ጌታን አገለግል ነበር። በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው። አሁንም እዚያ ስደርስ ምን እንደሚደርስብኝ ሳላውቅ በመንፈስ ቅዱስ ታዝዤ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዴ ነው። ይሁን እንጂ በየከተማው እስራትና ችግር እንደሚገጥመኝ መንፈስ ቅዱስ ነግሮኛል። የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም። “እስከ አሁን በእናንተ ሁሉ መካከል እየተዘዋወርኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እሰብክ ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ከእናንተ ማንም ከቶ ፊቴን እንደማያይ ዐውቃለሁ። ስለዚህ ከእናንተ አንድ እንኳ ቢጠፋ ኀላፊነት እንደሌለብኝ በዛሬው ቀን አስገነዝባችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ ምንም ያስቀረሁባችሁ ነገር የለም። መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ። እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ። ስለዚህ እያንዳንዳችሁን ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን እንባዬን እያፈሰስኩ እንደ መከርኳችሁ እያስታወሳችሁ ተጠንቀቁ። “አሁንም ሊያንጻችሁና በቅዱሳንም መካከል ርስት ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለእግዚአብሔርና ለጸጋው ቃልም ዐደራ ሰጥቼአለሁ። እኔ የማንንም ብር፥ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም። በገዛ እጆቼ እየሠራሁ ራሴንም ሆነ ጓደኞቼን እረዳ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።” ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ። ሁሉም አለቀሱና ጳውሎስን ዐቅፈው ሳሙት። ይልቁንም በጣም ያዘኑት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም” ብሎአቸው ስለ ነበር ነው፤ እስከ መርከብ ድረስም ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:4-38 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሸኙትም የቤርያው ሶጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤ እነዚህም ወደ ፊታችን አልፈው በጢሮአዳ ቆዩን። እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን። ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፤ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ። ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅፎም “ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ፤” አላቸው። ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪ ነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ። ብላቴናውንም ደኅና ሆኖ ወሰዱት፤ እጅግም ተጽናኑ። እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና። በአሶንም ባገኘን ጊዜ ተቀብለነው ወደ ሚጢሊኒ መጣን፤ በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፤ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና፤ ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተ ክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤ ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሤራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤ በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው። አሁንም እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ‘እስራትና መከራ ይቆይሃል፤’ ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል። ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። አሁንም እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፤ ምንም አላስቀረሁባችሁም። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ። ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።” ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤ ይልቁንም “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም፤” ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።