የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዋርያት ሥራ 20:15-38

ሐዋርያት ሥራ 20:15-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በማ​ግ​ሥ​ቱም ከዚያ ወጥ​ተን በኪ​ዮስ ፊት ለፊት ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሳሞስ አለ​ፍን፤ በት​ሮ​ጊ​ሊ​ዮም ተቀ​መ​ጥን፤ ከዚህ ቀን በኋ​ላም ወደ መሊጡ ደረ​ስን። ጳው​ሎ​ስም በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ በኤ​ፌ​ሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚ​ቻ​ለ​ውም ቢሆን ለበ​ዓለ ኀምሳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ድ​ረስ ቸኵሎ ነበ​ርና። ከመ​ሊ​ጡም የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን ቀሳ​ው​ስት ይጠ​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ኤፌ​ሶን ላከ። ወደ እር​ሱም በመጡ ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወደ እስያ ከገ​ባ​ሁ​በት ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ጀምሮ በዘ​መኑ ሁሉ ከእ​ና​ንተ ዘንድ እንደ ተቀ​መ​ጥሁ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ገ​ለ​ገ​ልሁ በፍ​ጹም መከ​ራና በል​ቅሶ ከአ​ይ​ሁ​ድም ሴራ የተ​ነሣ በደ​ረ​ሰ​ብኝ ፈተና እየ​ተ​ጋ​ደ​ልሁ፥ በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤ አሁ​ንም እነሆ በመ​ን​ፈስ ታሥሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን በዚያ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝን አላ​ው​ቅም። ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ፦ በየ​ከ​ተ​ማው መከ​ራና እስ​ራት ይጠ​ብ​ቅ​ሃል ብሎ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል። ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ወን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ሩጫ​ዬን እን​ድ​ጨ​ር​ስና መል​እ​ክ​ቴ​ንም እን​ድ​ፈ​ጽም ነው እንጂ ለሰ​ው​ነቴ ምንም አላ​ስ​ብ​ላ​ትም። አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ። እኔ ከሁ​ላ​ች​ሁም ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ እነሆ ዛሬ በዚች ሌሊት እመ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ኋ​ለሁ። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም። አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ። ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ። ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ። ስለ​ዚ​ህም ትጉ፤ እኔ ሁላ​ች​ሁ​ንም ሳስ​ተ​ምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እን​ባዬ እን​ዳ​ል​ተ​ገታ ዐስቡ። አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ሊያ​ን​ጻ​ችሁ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም ሁሉ መካ​ከል ርስ​ትን ሊሰ​ጣ​ችሁ ለሚ​ች​ለው ለጸ​ጋው ቃል አደራ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ። ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። እነ​ዚ​ህም እጆች ለም​ሻው ነገ​ርና ከእ​ኔም ጋር ላሉት እን​ዳ​ገ​ለ​ገሉ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።” ይህ​ንም ከአለ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ አብ​ረ​ውት ካሉት ሁሉ ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት። ይል​ቁ​ንም “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን አታ​ዩ​ትም” ስለ አላ​ቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መር​ከ​ብም ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:15-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በማግስቱም በመርከብ ተጕዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን። ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ አምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ። በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ አውራጃ ከገባሁባት ከመጀመሪያዋ ዕለት አንሥቶ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርሁ ታውቃላችሁ። ምንም እንኳ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ መከራ ቢያደርሱብኝም፣ ጌታን በታላቅ ትሕትናና በእንባ ከማገልገል አልተቈጠብሁም፤ በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም። በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ። “አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው። ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት። “አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ። ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚህች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና። ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ። እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሰርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ። ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ። ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ምንም ያህል ሳላቋርጥ በእንባ እያንዳንዳችሁን እንደ መከርኋችሁ አስታውሱ። “አሁንም ለእግዚአብሔር፣ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ። የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። በጕልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።” ይህን ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም ዐንገቱን ዐቅፈው ሳሙት። ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:15-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፥ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤ ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሴራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም። አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፥ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደ ሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ፦ እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል። ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ። ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ። ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤ ይልቁንም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:15-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በማግስቱ ከዚያ ተነሥተን በኪዮስ ፊት ለፊት ወዳለው ስፍራ በመርከብ ደረስን፤ በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞስ ተሻገርንና በማግስቱ ወደ ሚሊጢ ደረስን። ጳውሎስ በእስያ ጊዜ እንዳያባክን ብሎ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ፈለገ፤ ይህንንም ያደረገው ለጰንጠቆስጤ በዓል በኢየሩሳሌም ለመገኘት አስቦ ስለ ነበር ነው። ጳውሎስ ከሚሊጢ ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን አስጠራ፤ ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እስያ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤ በአይሁድ ሤራ ምክንያት መከራ ቢደርስብኝም እንኳ በፍጹም ትሕትናና በእንባ ጌታን አገለግል ነበር። በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው። አሁንም እዚያ ስደርስ ምን እንደሚደርስብኝ ሳላውቅ በመንፈስ ቅዱስ ታዝዤ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዴ ነው። ይሁን እንጂ በየከተማው እስራትና ችግር እንደሚገጥመኝ መንፈስ ቅዱስ ነግሮኛል። የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም። “እስከ አሁን በእናንተ ሁሉ መካከል እየተዘዋወርኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እሰብክ ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ከእናንተ ማንም ከቶ ፊቴን እንደማያይ ዐውቃለሁ። ስለዚህ ከእናንተ አንድ እንኳ ቢጠፋ ኀላፊነት እንደሌለብኝ በዛሬው ቀን አስገነዝባችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ ምንም ያስቀረሁባችሁ ነገር የለም። መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ። እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ። ስለዚህ እያንዳንዳችሁን ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን እንባዬን እያፈሰስኩ እንደ መከርኳችሁ እያስታወሳችሁ ተጠንቀቁ። “አሁንም ሊያንጻችሁና በቅዱሳንም መካከል ርስት ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለእግዚአብሔርና ለጸጋው ቃልም ዐደራ ሰጥቼአለሁ። እኔ የማንንም ብር፥ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም። በገዛ እጆቼ እየሠራሁ ራሴንም ሆነ ጓደኞቼን እረዳ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።” ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ። ሁሉም አለቀሱና ጳውሎስን ዐቅፈው ሳሙት። ይልቁንም በጣም ያዘኑት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም” ብሎአቸው ስለ ነበር ነው፤ እስከ መርከብ ድረስም ሸኙት።

ሐዋርያት ሥራ 20:15-38 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፤ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና፤ ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና። ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተ ክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤ ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሤራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤ በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው። አሁንም እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ‘እስራትና መከራ ይቆይሃል፤’ ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል። ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። አሁንም እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ። የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፤ ምንም አላስቀረሁባችሁም። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ። ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ። አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።” ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ። ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤ ይልቁንም “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም፤” ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።