ሐዋርያት ሥራ 14:23-28
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው። በጲስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፥ በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ፥ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ። በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ፣ በጾምና በጸሎት ላመኑበት ጌታ ዐደራ ሰጧቸው። በጲስድያም ዐልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፤ በጴርጌንም ቃሉን ከሰበኩ በኋላ፣ ወደ አጣልያ ወረዱ። ከአጣልያም፣ እስካሁን ላከናወኑት ሥራ፣ ለእግዚአብሔር ጸጋ በዐደራ ወደ ተሰጡባት ከተማ ወደ አንጾኪያ በመርከብ ተመለሱ። እዚያም በደረሱ ጊዜ፣ ቤተ ክርስቲያንን በአንድነት ሰብስበው፣ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት ያደረገውን ሁሉ፣ ደግሞም ለአሕዛብ እንዴት የእምነትን በር እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። በዚያም ከደቀ መዛሙርት ጋራ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለቤተ ክርስቲያንም ቀሳውስትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለዩም፤ ለሚታመኑበት ለእግዚአብሔርም አደራ ሰጡአቸው። ከጲስድያም ዐልፈው ጵንፍልያ ደረሱ። ጴርጌን በተባለችው ከተማም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ ኢጣሊያ ወረዱ። ከዚያም ስለሚሠሩት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ። አንጾኪያም በደረሱ ጊዜ ምእመናኑን ሁሉ ሰብስበው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ፥ ለአሕዛብም የሃይማኖትን በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው። ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ፣ በጾምና በጸሎት ላመኑበት ጌታ ዐደራ ሰጧቸው። በጲስድያም ዐልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፤ በጴርጌንም ቃሉን ከሰበኩ በኋላ፣ ወደ አጣልያ ወረዱ። ከአጣልያም፣ እስካሁን ላከናወኑት ሥራ፣ ለእግዚአብሔር ጸጋ በዐደራ ወደ ተሰጡባት ከተማ ወደ አንጾኪያ በመርከብ ተመለሱ። እዚያም በደረሱ ጊዜ፣ ቤተ ክርስቲያንን በአንድነት ሰብስበው፣ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት ያደረገውን ሁሉ፣ ደግሞም ለአሕዛብ እንዴት የእምነትን በር እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። በዚያም ከደቀ መዛሙርት ጋራ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው። በጲስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፥ በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ፥ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ። በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ሾሙላቸው፤ ከጾሙና ከጸለዩም በኋላ ላመኑበት ጌታ ዐደራ ሰጡአቸው። በጵስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ ሄዱ፤ በጴርጌም የእግዚአብሔርን ቃል ካስተማሩ በኋላ ወደ አጣልያ ሄዱ፤ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ ዐደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ። እዚያም በደረሱ ጊዜ አማኞችን በአንድነት ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያደረገውን ሁሉና አሕዛብም እንዲያምኑ እንዴት አድርጎ በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው። እዚያም ከአማኞች ጋር ብዙ ጊዜ ቈዩ።
ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው። በጲስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፤ በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ፤ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ። በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።