ሐዋርያት ሥራ 1:13-14
ሐዋርያት ሥራ 1:13-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ ከተማዪቱም በገቡ ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፤ እነዚህም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናኢ የተባለው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ከሴቶቹና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ጋር እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር በአንድ ልብ ሆነው ያለ ማቋረጥ ተግተው ይጸልዩ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 1:13-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም። እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 1:13-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ወደሚኖሩበት ሰገነት ላይ ወጡ፤ እነርሱም “ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ በርተሎሜዎስ፥ ማቴዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” ናቸው። እነዚህ ሁሉ ዘወትር ለጸሎት በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ ከእነርሱም ጋር አንዳንድ ሴቶችና የኢየሱስ እናት ማርያም፥ እንዲሁም የኢየሱስ ወንድሞች ነበሩ።
ሐዋርያት ሥራ 1:13-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ማደሪያቸውም በደረሱ ጊዜ ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴዎስ፥ በርተሎሜዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖን፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ። እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከጌታችን ከኢየሱስ እናት ከማርያም፥ ከወንድሞቹም ጋር በአንድነት ለጸሎት ይተጉ ነበር።