2 ሳሙኤል 3:2-5
2 ሳሙኤል 3:2-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለዳዊትም ወንዶች ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፤ በኵሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ። ሁለተኛውም ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቤግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌድሶር ንጉሥ ከቶልሜልም ልጅ ከመዓክ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ። አራተኛውም የአጊት ልጅ አዶንያስ፥ አምስተኛውም የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ ነበረ። ስድስተኛውም የዳዊት ሚስት የዒገል ልጅ ይትረኃም ነበረ። ለዳዊት በኬብሮን የተወለዱለት እነዚህ ነበሩ።
2 ሳሙኤል 3:2-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዳዊት በኬብሮን ሳለ፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኵር ልጁ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን፣ ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ፣ ሦስተኛው፣ ተልማይ ከተባለው ከጌሹር ንጉሥ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣ አራተኛው፣ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ አምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም ነበር፤ እነዚህ ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
2 ሳሙኤል 3:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለዳዊትም ወንድ ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፥ በኩሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ። ሁለተኛውም የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረች ከአቢግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ። አራተኛውም የአጊት ልጅ አዶንያስ፥ አምስተኛውም የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ ነበረ። ስድስተኛውም የዳዊት ልጅ ሚስት የዔግላ ልጅ ይትረኃም ነበረ። እነዚህም ለዳዊት በኬብሮን ተወለዱለት።
2 ሳሙኤል 3:2-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ዳዊት በኬብሮን ሳለ ስድስት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው ታልማይ ተብሎ የሚጠራው የገሹር ንጉሥ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶኒያ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፥ እነዚህ ሁሉ በኬብሮን የተወለዱ ናቸው።
2 ሳሙኤል 3:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ዳዊት በኬብሮን እያለ፥ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኲር ልጁ፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው፥ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው፥ ተልማይ ከተባለው ከገሹር ንጉሥ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው፥ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ አምስተኛው፥ ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው፥ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትረዓም ነበር፤ እነዚህ ዳዊት በኬብሮን እያለ የተወለዱለት ናቸው።