2 ጴጥሮስ 2:1-10
2 ጴጥሮስ 2:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ። ብዙዎች አስነዋሪ ድርጊቶቻቸውን ይከተላሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የእውነት መንገድ ይሰደባል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን እየተስገበገቡ በፈጠራ ታሪካቸው ይበዘብዟችኋል። ፍርዳቸው ከጥንት ጀምሮ ዝግጁ ነው፤ መጥፊያቸውም አያንቀላፋም። እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ከጣላቸውና በጨለማ ጕድጓድ ለፍርድ ካስቀመጣቸው፣ የጽድቅ ሰባኪ የነበረውንም ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋራ አድኖ፣ ለቀድሞው ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣ ደግሞም ኀጢአት ለሚያደርጉ ሁሉ ምሳሌ እንዲሆኑ፣ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣ ጻድቅ የሆነውንና በዐመፀኞች ሴሰኛ ድርጊት እየተሣቀቀ የኖረውን ሎጥን ካዳነ፣ ያ ጻድቅ ሰው በእነርሱ መካከል ሲኖር በሚያየውና በሚሰማው ነገር ነፍሱ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ድርጊታቸው ብትጨነቅም፣ ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል። በተለይም በርኩስ ምኞት የሥጋ ፍላጎታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ ሰማያውያንን ፍጡራን ሲሳደቡ አይፈሩም፤
2 ጴጥሮስ 2:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል፤ በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም፤ ጥፋታቸውም አያንቀላፋም። እግዚአብሔር ኀጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥ ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዐመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤
2 ጴጥሮስ 2:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ። ብዙዎች አስነዋሪ ድርጊቶቻቸውን ይከተላሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የእውነት መንገድ ይሰደባል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን እየተስገበገቡ በፈጠራ ታሪካቸው ይበዘብዟችኋል። ፍርዳቸው ከጥንት ጀምሮ ዝግጁ ነው፤ መጥፊያቸውም አያንቀላፋም። እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ከጣላቸውና በጨለማ ጕድጓድ ለፍርድ ካስቀመጣቸው፣ የጽድቅ ሰባኪ የነበረውንም ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋራ አድኖ፣ ለቀድሞው ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣ ደግሞም ኀጢአት ለሚያደርጉ ሁሉ ምሳሌ እንዲሆኑ፣ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣ ጻድቅ የሆነውንና በዐመፀኞች ሴሰኛ ድርጊት እየተሣቀቀ የኖረውን ሎጥን ካዳነ፣ ያ ጻድቅ ሰው በእነርሱ መካከል ሲኖር በሚያየውና በሚሰማው ነገር ነፍሱ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ድርጊታቸው ብትጨነቅም፣ ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል። በተለይም በርኩስ ምኞት የሥጋ ፍላጎታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ ሰማያውያንን ፍጡራን ሲሳደቡ አይፈሩም፤
2 ጴጥሮስ 2:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም። እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥ ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤
2 ጴጥሮስ 2:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። በዚህ ዐይነት ብዙዎች የእነርሱን አሳፋሪ መንገድ ይከተላሉ፤ ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል! መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤ እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ሲያመጣ ራርቶ የቀድሞውን ዓለም አልማረውም፤ ደግሞም እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ሁሉ የመቀጣጫ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ፈረደባቸው፤ በሕገ ወጦች አሳፋሪ ድርጊት እየተሠቀቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤ ያም ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር። እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው። በተለይም እነዚያን ርኩስ የሆነውን የሥጋ ፍትወታቸውን የሚከተሉትንና የእግዚአብሔርን ሥልጣን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ደፋሮችና ትዕቢተኞች ስለ ሆኑ የሰማይ ሥልጣናትን ሲሳደቡ አይፈሩም።
2 ጴጥሮስ 2:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይኖራሉ፤ እነርሱም ጥፋትን የሚያስከትሉ ትምህርቶች አስርገው በማስገባት የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፥ በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋትን ያመጣሉ። እንዲሁም ብዙዎች ጸያፍ ምግባራቸውን ይከተሏቸዋል፤ በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል! እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ፥ ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ፥ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥ ኃጢአትንም እያደረጉ ላሉት ምሳሌ እንዲሆን፤ የሰዶምንና ገሞራን ከተማዎች አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ከፈረደባቸው፥ በዝሙት ሥራቸው ሲሳቀቅ የነበረውን ጻድቅ ሎጥን ካዳነ፤ ያ ጻድቅ ሰው፥ በመካከላቸው ሲኖር ዕለት ከዕለት የዐመፀኞችን ሴሰኛ ኑሮ እያየና እየሰማ በክፉ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን ቢያስጨንቅም፤ እንግዲህ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው፥ እንዲሁም በደለኞችን እንዴት በቅጣት ስር ለፍርድ ቀንም ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል። ይልቁንም በርኩስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን፥ ጌትነትንም የሚንቁትን፤ ደፋሮችና እምቢተኞች ስለ ሆኑ ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይፈሩም፤