2 ነገሥት 3:16-17
2 ነገሥት 3:16-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቈፍሩ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም፥ ከብቶቻችሁም፥ እንስሶቻችሁም፥ ትጠጣላችሁ።
2 ነገሥት 3:16-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፤ ‘በዚህ ሸለቆ ብዙ ጕድጓዶች ቈፍሩ።’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ነፋስም ሆነ ዝናብ አታዩም፤ ሸለቆው ግን በውሃ ይሞላል፤ እናንተ፣ የቀንድ ከብቶቻችሁና ሌሎች እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’
2 ነገሥት 3:16-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህም አለ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፍሩ።’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውሃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’