2 ቆሮንቶስ 6:11-13
2 ቆሮንቶስ 6:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእናንተ አፋችን የተከፈተ ነው፤ ልባችንም የሰፋ ነው። ከእናንተ የደረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእኛም በእናንተ ላይ የደረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በልባችሁ አዝናችኋል። ልጆች እንደ መሆናችሁ፥ ይህን እላችኋለሁ፤ ከእናንተ ላይ ስለሚገባኝ ብድራቴ እናንተ ፍቅራችሁን አስፉልኝ።
Share
2 ቆሮንቶስ 6 ያንብቡ2 ቆሮንቶስ 6:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፤ ሁሉን በግልጽ ነግረናችኋል፤ ልባችንንም ወለል አድርገን ከፍተንላችኋል። ፍቅራችሁን የነፈጋችሁን እናንተ ናችሁ እንጂ እኛስ ፍቅራችንን አልነፈግናችሁም። ልጆቼ እንደ መሆናችሁ መጠን ይህን አሳስባችኋለሁ፤ እናንተም በዚያው ልክ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።
Share
2 ቆሮንቶስ 6 ያንብቡ2 ቆሮንቶስ 6:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እናንተ የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ አፋችን ለእናንተ ተከፍቶአል ልባችንም ሰፍቶላችኋል፤ በእኛ አልጠበባችሁም በሆዳችሁ ግን ጠቦባችኋል፤ ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን እላችኋለሁ፥ እናንተ ደግሞ ብድራት መልሳችሁልን ተስፋፉ።
Share
2 ቆሮንቶስ 6 ያንብቡ