2 ቆሮንቶስ 6:1-2
2 ቆሮንቶስ 6:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከእርሱም ጋር አብረን እየሠራን፥ የተቀበላችኋትን የእግዚአብሔር ጸጋ ለከንቱ እንዳታደርጓት እንማልዳችኋለን። እንዲህ ብሎአልና፥ “በተመረጠችው ቀን ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ” እነሆ፥ የተመረጠችው ቀን ዛሬ ናት።
2 ቆሮንቶስ 6:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከእግዚአብሔር ጋራ ዐብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን መጠን፣ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከንቱ እንዳታደርጉት ዐደራ እንላችኋለን። እርሱ፣ “በተወደደ ጊዜ ሰማሁህ፤ በድነት ቀን ረዳሁህ” ይላልና። እነሆ፤ የተወደደው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።
2 ቆሮንቶስ 6:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።