2 ቆሮንቶስ 5:5-8
2 ቆሮንቶስ 5:5-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ ሰጠን። እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ፥ ጨክኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ፤ ከሥጋችሁም ተለይታችሁ ወደ ጌታችን ትሄዳላችሁ። በእምነት እንኖራለን፤ በማየትም አይደለም። ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል።
2 ቆሮንቶስ 5:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለዚህ ዐላማ ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ሊመጣ ላለው ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን መያዣ አድርጎ የሰጠንም እርሱ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤ ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም። ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋር መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።
2 ቆሮንቶስ 5:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን። እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል።
2 ቆሮንቶስ 5:5-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ለዚህም ነገር ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ከዚያም በላይ ለሚሰጠን ነገር ሁሉ ዋስትና እንዲሆን መንፈሱን የሰጠንም እርሱ ነው። በምድራዊ ሰውነታችን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ከጌታ የራቅን መሆናችንን ብናውቅም እንኳ ሁልጊዜ በእርሱ እንተማመናለን። እኛ የምንኖረውም ጌታን በማመን እንጂ እርሱን በማየት አይደለም። ከዚህ እንደ መኖሪያችን ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር ለመሆን እንመኛለን፤ ስለዚህ በመተማመን እንኖራለን።