1 ሳሙኤል 9:21 - Compare All Versions
1 ሳሙኤል 9:21 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ሳኦልም መልሶ፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ ሰው አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ?” አለ።
1 ሳሙኤል 9:21 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ሳኦልም፣ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ጐሣዬስ ከብንያም ነገድ ጐሣዎች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለ ምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።
1 ሳሙኤል 9:21 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሳኦልም መልሶ፦ እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ? አለ።
1 ሳሙኤል 9:21 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ሳኦልም “እኔ ከእስራኤል ነገዶች መካከል በተለይ ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ተወላጅ ነኝ፤ በዚሁም ነገድ ውስጥ እንኳ የእኔ ቤተሰብ በጣም አነስተኛ ነው፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለእኔ ስለምን ትነግረኛለህ?” ሲል መለሰለት።
1 ሳሙኤል 9:21 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ሳኦልም፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።