የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ሳሙኤል 7:10-14

1 ሳሙኤል 7:10-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሳሙ​ኤ​ልም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሲያ​ሣ​ርግ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ቀን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ታላቅ የነ​ጐ​ድ​ጓድ ድምፅ አን​ጐ​ደ​ጐደ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ፊት ድል ተመቱ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከመ​ሴፋ ወጡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አሳ​ደዱ፤ በቤ​ኮር ታችም እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ መቱ​አ​ቸው። ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ዳግ​መ​ኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስ​ራ​ኤል ድን​በር አል​ወ​ጡም፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ነበ​ረች። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከአ​ስ​ቀ​ሎና ጀምሮ እስከ፤ ጌት ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ተመ​ለሱ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ድን​በ​ሩን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ወሰዱ። በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በአ​ሞ​ራ​ው​ያን መካ​ከ​ልም ሰላም ሆነ።

1 ሳሙኤል 7:10-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ይሁን እንጂ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ ስላንጐዳጐደባቸው እጅግ ተሸበሩ፤ ድልም ተመተው ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ። እስራኤላውያንም ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጥኤማውያንን በየመንገዱ እየገደሉ ከቤትካር በታች እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዷቸው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ ስሙንም “እግዚአብሔር እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው። በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለ ተመቱ፣ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር። ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ነበረ።

1 ሳሙኤል 7:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሳሙኤልም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሲያሳርግ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፥ እግዚአብሔርም በዚያች ቀን በፍልስጥኤማውያን ላይ ታላቅ ነጎድጓድ አንጎደጎደ፥ አስደነገጣቸውም፥ በእስራኤልም ፊት ድል ተመቱ። የእስራኤልም ሰዎች ከምጽጳ ወጡ፥ ፍልስጥኤማውያንንም አሳደዱ፥ በቤትካር ታችም እስኪደርሱ ድረስ መቱአቸው። ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፥ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው። ፍልስጥኤማውያንም ተዋረዱ፥ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፥ በሳሙኤል ዕድሜ ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች። ፍልስጥኤማውያንም ከአስቀሎና ጀምሮ እስከ ጌት ድረስ ከእስራኤል የወሰዱአቸው ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱ፥ እስራኤልም ድንበሩን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳነ። በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ዕርቅ ነበረ።

1 ሳሙኤል 7:10-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በማቅረብ ላይ ሳለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ዘመቱ፤ ነገር ግን በዚያች ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከፍተኛ ነጐድጓድ አንጐድጒዶ አርበደበዳቸው፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ። እስራኤላውያንም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ቤትካር በታች እያሳደዱ በየመንገዱ ገደሉአቸው። ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል ተከለው፦ እግዚአብሔር እስካሁን ረድቶናል ለማለት ስሙን አቤንዔዜር ብሎ ሰየመው። በዚህም ዐይነት ፍልስጥኤማውያን ድል ተመቱ። ሳሙኤል በኖረበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያን ዳግመኛ ወደ እስራኤል ድንበር አልቀረቡም። ፍልስጥኤማውያን የያዙአቸው በዔቅሮንና በጋት መካከል የነበሩትም ከተሞች ሁሉ ለእስራኤላውያን ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያንም ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳኑ፤ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከልም ዕርቀ ሰላም ወርዶ ነበር።

1 ሳሙኤል 7:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፥ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ጌታ ግን በዚያ ዕለት በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ አንጐዳጐደባቸው፤ እነርሱም እጅግ ተሸበሩ፤ በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመተውም ሸሹ። እስራኤላውያንም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ቤትካር በታች እያሳደዱ በየመንገዱ ገደሉአቸው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ “ጌታ እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል ስሙን “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው። በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለተመቱ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ የጌታ እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች። ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከዔቅሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ወርዶ ነበር።