የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ሳሙኤል 17:40-45

1 ሳሙኤል 17:40-45 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር። ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን አለው፥ “አንተ ሰይ​ፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመ​ጣ​ብ​ኛ​ለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው በእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች አም​ላክ ስም በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።