የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ነገሥት 18:1-8

1 ነገሥት 18:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከብዙ ቀንም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት፥ “ሂድ ለአ​ክ​ዓብ ተገ​ለጥ፤ በም​ድር ላይም ዝናም እሰ​ጣ​ለሁ” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ። ኤል​ያ​ስም ለአ​ክ​ዓብ ይገ​ለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ራብ ጸንቶ ነበር። አክ​ዓ​ብም የቤ​ቱን አዛዢ አብ​ድ​ዩን ጠራ፤ አብ​ድ​ዩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ይፈራ ነበር። ኤል​ዛ​ቤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነቢ​ያት ባስ​ገ​ደ​ለች ጊዜ አብ​ድዩ መቶ​ውን ነቢ​ያት ወስዶ አምሳ አም​ሳ​ውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እን​ጀ​ራና ውኃ ይመ​ግ​ባ​ቸው ነበር። አክ​ዓ​ብም አብ​ድ​ዩን፥ “በሀ​ገሩ መካ​ከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እን​ሂድ፤ እን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ችን የም​ና​ድ​ን​በት ሣር ምና​ል​ባት እና​ገኝ እንደ ሆነ” አለው። በመ​ን​ገ​ድም ተለ​ያ​ይ​ተው ሄዱ፤ አክ​ዓ​ብም ለብ​ቻው በአ​ንድ መን​ገድ፥ አብ​ድ​ዩም ለብ​ቻው በሌላ መን​ገድ ሄዱ። አብ​ድ​ዩም በመ​ን​ገድ ብቻ​ውን ሳለ እነሆ፥ ኤል​ያስ ሊገ​ና​ኘው ብቻ​ውን መጣ፤ አብ​ድ​ዩም ሮጠና፥ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኤል​ያስ አንተ ነህን?” አለው። ኤል​ያ​ስም፥ “አዎ እኔ ነኝ ሄደህ ለጌ​ታህ፦ እነሆ፥ ኤል​ያስ በዚህ አለ በል” አለው።

1 ነገሥት 18:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከብዙ ጊዜ በኋላም በሦስተኛው ዓመት እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ለኤልያስ መጣለት፤ “ሄደህ ለአክዓብ ተገለጥ፤ እኔም በምድሪቱ ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።” ስለዚህም ኤልያስ ራሱን በአክዓብ ፊት ለመግለጥ ሄደ። በዚህ ጊዜ ራብ በሰማርያ ክፋኛ ጸንቶ ነበር። አክዓብም የቤተ መንግሥቱን አዛዥ አብድዩን ጠራው፤ አብድዩም እግዚአብሔርን በጣም የሚፈራ ሰው ነበር። ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያስገደለች በነበረበት ጊዜ፣ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በሁለት ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይሰጣቸው ነበር። አክዓብም አብድዩን፣ “ተነሣና በአገሪቱ ውስጥ ወዳሉት ምንጮችና ሸለቆዎች ሂድ፤ ፈረሶቻችንና በቅሎዎቻችን እንዳይሞቱ በሕይወት እንዲቈዩ ምናልባት ሣር እናገኝ ይሆናል።” አለው። ስለዚህ የሚሄዱበትን ምድር ተከፋፈሉ፤ አክዓብ በአንድ በኩል፣ አብድዩም በሌላ በኩል ሄደ። አብድዩ በመንገድ ላይ ሳለም ኤልያስን አገኘው። አብድዩም ዐወቀው፤ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት፣ “ጌታዬ ኤልያስ ሆይ፤ በርግጥ አንተ ነህን?” አለው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ፤ ሂድና ለጌታህ፣ ‘ኤልያስ እዚሁ አለልህ’ ብለህ ንገረው” ሲል መለሰለት።

1 ነገሥት 18:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከብዙ ቀንም በኋላ በሦስተኛውም ዓመት “ሂድ፤ ለአክዓብ ተገለጥ፤ በምድር ላይም ዝናብ እሰጣለሁ፤” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ። ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰማርያም ራብ ጸንቶ ነበር። አክዓብም የቤቱን አዛዥ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር። ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ እርሱ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይመግባቸው ነበር። አክዓብም አብድዩን “በአገሩ መካከል ወደ ውሃው ምንጭ ሁሉና ወደ ወንዝ ሁሉ ሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኛለን፤” አለው። ሁለቱም የሚሄዱበትን አገር ተካፈሉ፤ አክዓብም ለብቻው በአንድ መንገድ አብድዩም ለብቻው በሌላ መንገድ ሄዱ። አብድዩም በመንገድ ሲሄድ፥ እነሆ፥ ኤልያስ ተገናኘው፤ አብድዩም አወቀው፤ በግምባሩም ተደፍቶ “ጌታዬ ሆይ! ኤልያስ አንተ ነህን?” አለ። ኤልያስም “እኔ ነኝ፤ ሄደህ ለጌታህ ‘ኤልያስ ተገኝቶአል፤’ በል፤” አለው።

1 ነገሥት 18:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት እግዚአብሔር ኤልያስን “ሄደህ ራስህን ለንጉሥ አክዓብ ግለጥለት፤ እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ” አለው፤ ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አክዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሀብ እጅግ ጸንቶ ነበር። ስለዚህም ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነው፤ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር። አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው። እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳለባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ። አብድዩ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሳለ በድንገት ኤልያስን አገኘው፤ ኤልያስ መሆኑንም ስላወቀ በግንባሩ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ከነሣው በኋላ “ጌታዬ ኤልያስ! በእውነት አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ኤልያስም “አዎ! እኔ ነኝ፤ እዚህ መሆኔን ሄደህ ለጌታህ ንገረው” ሲል መለሰለት።

1 ነገሥት 18:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት ጌታ ኤልያስን “ሄደህ ራስህን ለንጉሥ አክዓብ ግለጥለት፤ እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ” አለው። ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አክዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሀብ እጅግ ጸንቶ ነበር። ስለዚህም ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ ጌታን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነው። ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር። አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው። እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳለባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ። አብድዩ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሳለ በድንገት ኤልያስን አገኘው፤ ኤልያስ መሆኑንም ስላወቀ በግንባሩ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ከነሣው በኋላ “ጌታዬ ኤልያስ! በእውነት አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ኤልያስም “አዎ! እኔ ነኝ፤ እዚህ መሆኔን ሄደህ ለጌታህ ንገረው” ሲል መለሰለት።