1 ዮሐንስ 3:1-7

1 ዮሐንስ 3:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ! በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን። ይህ እንደሚሆን በክርስቶስ ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ ክርስቶስ ንጹሕ እንደ ሆነ እርሱም ራሱን ንጹሕ ያደርጋል። ኃጢአት ማለት የእግዚአብሔርን ሕግ ማፍረስ ስለ ሆነ ኃጢአትን የሚሠራ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ያፈርሳል። ክርስቶስ የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ እንደ ተገለጠና እርሱም ኃጢአት እንደሌለበት ታውቃላችሁ። ስለዚህ በክርስቶስ የሚኖር ሰው ሁሉ ኃጢአት አይሠራም። ኃጢአት የሚሠራም ሰው ክርስቶስን አላየውም ወይም አላወቀውም። ልጆች ሆይ! ማንም አያታላችሁ፤ ክርስቶስ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ጻድቅ ነው።

1 ዮሐንስ 3:1-7

1 ዮሐንስ 3:1-7 NASV