የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ቆሮንቶስ 12:12-18

1 ቆሮንቶስ 12:12-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎ​ችም እንደ አሉ​በት፥ ነገር ግን የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ብዙ​ዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክር​ስ​ቶስ ደግሞ እን​ዲሁ ነው፤ እኛ ሁላ​ች​ንም በአ​ንድ መን​ፈስ አንድ አካል ለመ​ሆን ተጠ​ም​ቀ​ናል፤ አይ​ሁድ ብን​ሆን፥ አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብን​ሆን፥ ባሪ​ያ​ዎ​ችም ብን​ሆን፥ ነጻ​ዎ​ችም ብን​ሆን ሁላ​ችን አንድ መን​ፈስ ጠጥ​ተ​ና​ልና። የአ​ካ​ላ​ች​ንም ክፍሉ ብዙ ነው እንጂ አንድ አይ​ደ​ለም። እግ​ርም፥ “እኔ እጅ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን? ጆሮም፥ “እኔ ዐይን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን? አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ መስ​ማት ከየት በተ​ገኘ ነበር፤ አካ​ልስ ሁሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ ማሽ​ተት ከየት በተ​ገኘ ነበር? አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ካ​ላ​ች​ንን ክፍል በሰ​ው​ነ​ታ​ችን ውስጥ እርሱ እንደ ወደደ እየ​ራሱ አከ​ና​ውኖ መደ​በው።

1 ቆሮንቶስ 12:12-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አንድ ሰው ብዙ የአካል ክፍሎች አሉት፤ የአካል ክፍሎች ብዙዎች ሆነው ሳሉ የሚገኙት በዚያው በአንዱ አካል ነው። እንዲሁም ክርስቶስ ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉት እንደ አንድ አካል ነው። አይሁድም ብንሆን የግሪክ ሰዎች ብንሆን፤ ባሪያዎችም ብንሆን፥ ነጻ ሰዎችም ብንሆን፥ አንድ ሰውነት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል፤ ሁላችንም ከዚሁ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተናል። አንድ አካል የተሠራው ከብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ ከአንድ የአካል ክፍል ብቻ አይደለም! እግር “እኔ እጅ ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም!” ቢል ታዲያ እንዲህ በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? ጆሮም “እኔ ዐይን ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል፥ ታዲያ፥ እንዲህ በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? አንድ አካል በሙሉ ዐይን ብቻ ቢሆን ኖሮ በምን መስማት ይቻል ነበር? አንድ አካል በሙሉ ጆሮ ብቻ ቢሆን ኖሮ በምን ማሽተት ይቻል ነበር? አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ፈለገው እያንዳንዱን የአካል ክፍል በአካል ውስጥ ተገቢ ስፍራውን ይዞ እንዲገኝ አድርጎታል።