1 ቆሮንቶስ 12:1-4
1 ቆሮንቶስ 12:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወንድሞች ሆይ፤ አሁን ደግሞ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይህን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። አረማውያን በነበራችሁበት ጊዜ ወዲያና ወዲህ በመነዳት ድዳ ወደ ሆኑ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ። ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ የሚናገር፣ “ኢየሱስ የተረገመ ነው” የሚል የለም፤ እንደዚሁም በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር፣ ማንም “ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚል እንደሌለ እነግራችኋለሁ። ስጦታዎች ልዩ ልዩ ሲሆኑ፣ መንፈስ ግን አንድ ነው፤
1 ቆሮንቶስ 12:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ወንድሞቼ ሆይ! አሁን ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እንድታውቁ እፈልጋለሁ። አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ በማታውቁት ነገር ተመርታችሁ መናገር ወደማይችሉ ጣዖቶች ትወሰዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ። ስለዚህ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ኢየሱስን የሚረግም ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው!” የሚል ማንም እንደሌለ እነግራችኋለሁ። ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አሉ፤ መንፈስ ቅዱስ ግን አንድ ነው።
1 ቆሮንቶስ 12:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አላዋቆች ልትሆኑ አንወድድም። ቀድሞም እናንተ አሕዛብ በነበራችሁ ጊዜ ዲዳዎች ጣዖታትን ታመልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖትም በማምለክ ረክሳችሁ እንደ ነበር፥ ወደ ወሰዱአችሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ። ስለዚህም ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፥ “ኢየሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው” ሊል አንድስ እንኳን እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦታው ልዩ ልዩ ነው።
1 ቆሮንቶስ 12:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አሕዛብ ሳላችሁ በማናቸውም ጊዜ እንደምትመሩ ድምፅ ወደሌላቸው ወደ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ። ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤
1 ቆሮንቶስ 12:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ! አላዋቂ እንድትሆኑ አልፈልግም። አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ በማታውቁት ነገር ተመርታችሁ መናገር ወደማይችሉ ጣዖቶች ትወሰዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ። ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር “ኢየሱስ የተረገመ ነው፤” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው፤” ሊል ማንም እንደማይችል አስታውቃችኋለሁ። ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፤ መንፈስ ግን አንድ ነው፤