መጽሐፈ ሩት 4:13-16
መጽሐፈ ሩት 4:13-16 አማ54
ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ደረስባትም፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፤ ወንድ ልጅም ወለደች። ሴቶችም ኑኃሚንን “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ስሙም በእስራኤል ይጠራ። ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፤ በእርጅናሽም ይመገባሻል፤” አሉአት። ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፤ ሞግዚትም ሆነችው።

