የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 37

37
1ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥
ከስፍራውም ተንቀሳቀሰ።
2የድምፁን መትመም ስሙ፥
ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ አድምጡ።
3እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥
ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል።
4በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፥
በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፥
ድምፁም በተሰማ ጊዜ
መብረቁን አይከለክልም።
5እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፥
እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
6በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ፦
በምድር ላይ ውደቁ ይላል።
7ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድ
የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል።
8አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥
በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
9ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥
ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።
10ከእግዚአብሔር እስትንፋስ ውርጭ ተሰጥቶአል፥
የውኆችም ስፋት ይጠብባል።
11የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፥
የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፥
12-13ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥
ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ
ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ
ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራል።
14ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥
ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።
15በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥
የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?
16ወይስ የደመናውን ሚዛን፥
ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?
17በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥
ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
18እንደ ቀለጠ መስተዋት
ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?
19እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና
የምንለውን አስታውቀን።
20ማንም በእርሱ ላይ ቢናገር ፈጽሞ ይዋጣልና
እኔ እናገር ዘንድ ብወድድ ሰው ይነግረዋልን?
21አሁንም ነፋስ አልፎ ካጠራቸው በኋላ፥
ሰው በሰማያት የሚበራውን ብርሃን ሊመለከት አይችልም።
22ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፥
በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።
23ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፥
በኃይል ታላቅ ነው፥
በፍርድና በጽድቅም አያስጨንቅም።
24ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፥
በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ