የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 14

14
1ከሴት የተወለደ ሰው
የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።
2እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም፥
እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።
3እንደዚህስ ባለ ሰው ላይ ዓይኖችህን ትከፍታለህን?
ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታገባለህን?
4ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል?
አንድ እንኳ የሚችል የለም።
5የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥
የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥
እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።
6እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ
ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።
7ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥
ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው።
8ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥
ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥
9ከውኃ ሽታ የተነሣ ያቈጠቍጣል፥
እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።
10ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥
ሰውም ነፍሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?
11ውኃ ከባሕር ውስጥ ያልቃል፥
ወንዙም ያንሳል ይደርቅማል።
12ሰውም ተኝቶ አይነሣም፥
ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥
ከእንቅልፉም አይነሣም።
13በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ!
ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ!
ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!
14በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን?
መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥
የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
15በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፥
የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።
16አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፥
ኃጢአቴንም ትጠባበቃለህ።
17መተላልፌ በከረጢት ውስጥ ታትሞአል፥
ኃጢአቴንም ለብጠህበታል።
18ተራራ ሲወድቅ ይጠፋል፥
ዓለቱም ከስፍራው ይፈልሳል፥
19ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥
ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥
እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።
20ለዘላለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥
ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ።
21ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፥
ቢዋረዱም አያይም።
22ነገር ግን የገዛ ሥጋው ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥
ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ