መጽሐፈ መሳፍንት 3:28-31

መጽሐፈ መሳፍንት 3:28-31 አማ54

እርሱም፦ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተከተሉኝ አላቸው። ተከትለውትም ወረዱ፥ ወደ ሞዓብም የሚያሻግረውን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ያዙ፥ ማንንም አላሳለፉም። የዚያን ጊዜም ከሞዓብ አሥር ሺህ የሚያህሉትን፥ ጎልማሶችና ጽኑዓን ሁሉ፥ መቱ፥ አንድ እንኳ አላመለጠም። በዚያም ቀን ሞዓብ ከእስራኤል እጅ በታች ተዋረደ፥ ምድሪቱም ሰማንያ ዓመት ዐረፈች። ከእርሱም በኋላ የዓናት ልጅ ሰሜጋር ተነሣ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፥ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።