ትንቢተ ሆሴዕ 13:1-6

ትንቢተ ሆሴዕ 13:1-6 አማ54

ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም ዘንድ ታበየ፥ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ። አሁንም ኃጢአትን ይሠሩ ዘንድ ጨመሩ፥ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፥ ሁሉም የሠራተኛ ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም፦ የሚሠው ሰዎች እምቦሳውን ይሳሙ ይላሉ። ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋትም እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፍስም ከአውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ። እኔ ግን ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ መድኃኒት የለም። በምድረ በዳ፥ እጅግ በደረቀ ምድር አውቄህ ነበር። ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ፥ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ፥ ስለዚህ ረሱኝ።