የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 6:1-22

ኦሪት ዘፍጥረት 6:1-22 አማ54

እንዲህም ሆነ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ። እግዚአብሔርም፤ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ። በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኂያላን ሆኑ። እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፤ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንድ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም አዘነ። እግዚአብሔርም፤ የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለ ፈጠርኍቸው ተጸጽቼእለሁና አለ። ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ። የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ስው ነበረ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረግ። ኖኅም ሦስት ልጆችን ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ። ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸ ምድርም ግፍን ተሞላች። እግዚአብሔርም ምድርን አየ፤ እነሆም ተበላሸች ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና። እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፤ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችን እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ በውስጥን በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት። እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፤ ወርድዋ አምሳ ክንድ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። ለመርከቢቱ መስኮትን ታድርጋለህ ከቁመትዋም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ ታችኛውንም ሁለተኛውንም ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ። እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኂን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል። ቃል ኪዳኔም ከአንተ ጋር አቆማለሁ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ። ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለር እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ ተባትና እንስት ይሁን። ከወፍ እንደ ወገኑ ከእንስሳም እንደ ወገኑ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንድ ወገኑ በሕይውር ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆን ወደ አንተ ይግቡ። ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል። ኖኅም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}