ኦሪት ዘፍጥረት 5:28-32

ኦሪት ዘፍጥረት 5:28-32 አማ54

ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ልጅንም ወለደ። ስሙንም፤ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኍላ የኖረው አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ ሞተም። ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}