የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 41:14-25

ኦሪት ዘፍጥረት 41:14-25 አማ54

ፈርዖንም ልኮ ዮሴፍን አስጠራ ከግዞት ቤትም አስቸኮሉት፤ እርሱም ተላጨ ልብሱንም ለወጠ፥ ወደ ፈርዖን ገባ። ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ ሕልምን አየሁ የሚተረጕመውም አልተገኘም ሕልምን እንደ ሰማህ እንደ ተረጎምህም ስለ አንተ ሰማሁ። ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ይህ በእኔ አይደለም እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በደኅንነት ይመልስለታል። ፈርዖንም ለዮሴፍ እንዲህ አለው፦ እነሆ በሕልሜ በወንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ እነሆም ሥጋቸውም የወፈረ መልካቸውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ በመስኩም ይስማሩ ነበር። ከእነርሱን በኍላ እነሆ የደከሙ መልካቸውም እጅግ የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ በግብፅም ምድር ሁሉ እንደ እነርሱ መልክ ከፍ ከቶ አላየሁም፤ የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ወፍራሞቹን ስባት ላሞች ዋጡአቸው፥ በሆዳቸውም ተዋጡ አልታወቀም መልካቸውም በመጀመሪያ እንደ ነበረውም የከፋ ነበረ። በሕልሜም እነሆ የዳበሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች በአንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ ከእነርሱም በኍላ እነሆ የደረቁና የሰለቱ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ስባት እሸቶች ወጡ የሰለቱት እሸቶች ያማሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ። ዮሴፍም ፈርዖንን አለው፦ የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን ነግሮታል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}