ኦሪት ዘፍጥረት 38:1-26

ኦሪት ዘፍጥረት 38:1-26 አማ54

በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወረድ፥ ስሙን ኤራስ ወደሚሉት ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው ገባ። ከዚያም ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ ወሰዳትም ወደ እርስዋም ገባ። ፀነሰችም ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙንም አውናን ብላ ጠራችው። እንደ ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው እርሱንም በወለደች ጊዜ ክዚብ በሚባል አገር ነበረች። ይሁዳም ለበኵር ልጁ ለዔርትዕማር የምትባል ሚስት አጋባው። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔር ቀሠፈው። ይሁዳም አውናን፦ ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ አግባትም ለወንድምህም ዘርን አቁምለት አለው። አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይስጥ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር። ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፋ ሆነበት፥ እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው። ይሁዳም ምራትን ትዕማርን፦ ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ አላት እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞት ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባትዋ ቤት ተቀመጠች። ከብዙ ዘመንም በኍላ የይሁዳ ሚስት የሴዋ ልጅ ሞተች ይሁዳም ተጽናና የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ እርሱም ዓዶሎማዊው ወዳጁም ኤራስ። ለትዕማርም፦ እነሆ አማትሽ ይሁዳ የበጎቹን ጠጕር ይሸልት ዘንድ ወደ ተምና ይወጣል ብለው ነገሩአት። እርስዋም የመበለትነትዋን ልብስ አወለቀች፥ መጎናጸፊያዋንም ወሰደች ተሸፈነችም ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች ሴሌም እንደ አደገ ሚስትም እንዳልሆነችው አይታለችና። ይሁዳም ባያት ጊዜ ጋለሞታን መሰለችው ፊትዋን ተሸፍና ነበርና። ወደ እርስዋም አዘነበለ፦ እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፦ ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ? አለችው። የፍየል ጠቦት ከመንጋዬ እሰድድልሻለሁ አላት። እርስዋም፦ እስክትሰደድልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህን? አለችው። እርሱም፦ ምን መያዣ ልስጥሽ? አላት። እርስዋም፦ ቀለበትህን አምባርህን በእጅህ ያለውን በትር አለች እርሱም ሰጣትና ከእርስዋ ደረሰ እርስዋም ፀነሰችለት። ኤስውም ተነሥታ ሄደች መጎናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነትዋን ልብስ ለበስች። ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በወዳጁ በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት እርስዋንም፥ አላገኛትም። እርሱም የአገሩን ሰዎች፦ በኤናይም በመንገድ ዳር ተቀምጣ የነበረች ጋለሞታ ወዴት ናት? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፦ በዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉት። ወደ ይሁዳም ተመልሶ እንዲህ አለው፦ አላገኘኍትም የአገሩም ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉኝ። ይሁዳም፦ እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው እነሆ የፍየሉን ጠቦት ሰደድሁላት አንተም አላገኘሃትም አለ። እንዲህም ሆን ከሦስት ወር በኍላ ለይሁዳ፦ ምራትህ ትዕማር ሴሰነች፤ ደግሞም በዝሙት እነሆ ፀነሰች ብለው ነገሩት። ይሁዳም፦ አውጡአትና በእሳት ትቃጠል አለ። እርስዋም ባወጡአት ጊዜ ወደ አማትዋ እንዲህ ብላ ላከች፦ ለዚህ ለባለ ገንዘብ ነው የፀነስሁት፤ ተመልከት፤ ይህ ቀለበት ይህ አምባር፤ ይህ በትር የማን ነው? ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነትኛ ሆነች ልጄን ሴሎምን አልሰጠኍትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}