ኦሪት ዘፍጥረት 37:5-28

ኦሪት ዘፍጥረት 37:5-28 አማ54

ዮሴፍም ሕልምን አለመ ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እነርሱም እንደ ገና በብዙ ጠሉት እርሱ አላቸው፦ እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፤ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና እነሆም የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ። ወንድሞቹም፦ በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን? አሉት። እንደ ገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ ይልቁን ጠሉት። ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እንዲህም አለ፦ እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ እነሆ ፀሐይን ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብርም ሲሰግዱልኝ አየሁ። ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው አባቱም ገሠጸው እንዲህም አለው፦ ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድር ነው? በውኑ እኔና እናትህ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንስገድልህ ይሆን? ወንድሞቹም ቀኑበት አባቱ ግን ነገሩን ይጠብቅው ነበር። ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ። እስራኤልም ዮሴፍን፦ ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና አለው። እርሱም እነሆኝ አለው። እርሱም፦ ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅን እንደ ሆኑ እይ ወሬአቸውንም አምጣክኝ አለው። እንዲንም ከኬብሮን ቆላ ሰደደው ወደ ሴኬምም መጣ። እነሆም በምድረ በዳ ስቅበዘብዝ ሳለ አንድ ሰው አገኘው ሰውዮውም፦ ምን ትፈልጋለህ? ብሎ ጠየቀው። እርሱም ወንድሞቼን እፈልጋለሁ በጎቹን የሚጠብቁበት ወዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ አለ። ሰውዮውም፦ ከዚህ ተነሥተዋል ወደ ዶታይን እንሂድ ሲሉም ስምቼአቸዋለሁ አለው። ዮሴፍም ወንድሞቹን ተከታትሎ ሄደ በዶታይንም አገኛቸው። እነርሱ በሩቅ ሳለ አዩት ወድ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ። አንዱም ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ያባለ ሕልም ይኸው መጣ። አሁንም ኑ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፦ ክፋ አውሬም በላው እንላለን ከሕልሞቹም የሚሆነውን እናያለን። ሮቤልም ይህን ሰማ ከእጃቸውም አዳነው እንዲህም አለ፦ ሕይወቱን አናጥፋ። ሮቤል፦ ደም አታፍስሱ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት አላቸው እንዲህም ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው። እንዲንም ሆነ ዮሴፍም ወደ ወንድሞቹ በቀረበ ጊዜ የለበሳትን በብዙ ኅብር ያጌጠቺቱ ቀሚሱን ገፈፋት ወስደውም ወደ ጕድጓድ ጣሉት ጕድጓዱም ውኃ የሌለበት ደረቅ ነበረ። እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ ዓይናቸውንም አንሥተው አዩ፥ እነሆም የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ መጡ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን ከርቤም ተጭነው ነበር። ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ ወንድማችንን ገድለን ደሙን ብንሸሽግ ጥቅማችን ምንድር ነውም? ኑ ለእስማኤላውያን እንሽጠው እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አንጣል፥ ወንድማችን ሥጋችንም ነውና የምድያም ነጋዶችም አለፈ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}