ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ። እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው። እንዲህም አለው፦ ስምህ ማን ነው? እርሱም፦ ያዕቆብ ነኝ አለው። አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና። ያዕቆብም፦ ስምህን ንገረኝ ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ዽኒኤል ብሎ ጠራው። ዽኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 32 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 32:24-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች