አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤ በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:13-22
9 ቀናት
ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
28 ቀናት
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች