ኦሪት ዘዳግም 33
33
1የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት። 2እንዲህም አለ፦ 2 እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ 2 በሴይርም ተገለጠ፤ 2 ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ 2 ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ 2 በስተቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው። 3ሕዝቡንም ወደዳቸው፤ 2 ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ 2 በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ 2 ቃሎችህን ይቀበላሉ። 4ሙሴ ለያዕቆብ ጉባኤ ርስት የሆነውን 2 ሕግ አዘዘን። 5የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች 2 ሁሉ ጋር በተከማቹ ጊዜ፥ 2 ንጉሥ በይሹሩን ነበረ። 6ሮቤል በህይወት ይኑር፥ አይሙት፤ 2 ሰዎቹም በቁጥር ብዙ ይሁኑ፤ 7የይሁዳ በረከት ይህ ነው፤ እንዲህም አለ፦ 2 አቤቱ፥ የይሁዳን ድምፅ ስማ፥ 2 ወደ ወገኖቹም አግባው፤ 2 እጆቹ ይጠንክሩለት፤ 2 በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ። 8ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፥ 2 ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ 2 በማሳህ ለፈተንኸው፥ 2 በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤ 9ስለ አባቱና ስለ እናቱ፦ አላየሁም ላለ፥ 2 ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ 2 ልጆቹንም ላላወቀ፤ 2 ቃልህን አደረጉ፥ 2 ቃል ኪዳንህንም ጠበቁ። 10ፍርድህን ለያዕቆብ፥ 2 ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ 2 በፊትህ ዕጣንን፥ 2 በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ይሠዋሉ። 11አቤቱ፥ ሀብቱን ባርክ፥ 2 የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ 2 የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፥ 2 የሚጠሉትም አይነሡ። 12ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ 2 በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ 2 ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ 2 ቀኑን ሁሉ ይጋርደዋል፥ 2 በትከሻውም መካከል ያድራል። 13ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ 2 ምድሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ 2 በሰማያት ገናንነት በጠል፥ 2 በታችኛውም ቀላይ፥ 14በፀሐዩ ፍሬያት ገናንነት፥ 2 በጨረቃውም መውጣት ገናንነት 15በቀደሙትም ተራሮች ከፍተኛነት፥ 2 በዘላለሙም ኮረብቶች ገናንነት፥ 16በምድሪቱም ገናንነትና ሞላዋ፥ 2 በቁጥቍጦው ውስጥ ከነበረው በረከት 2 በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በተለየው ራስ አናት ላይ ይውረድ። 17ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፤ 2 ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤ 2 በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን 2 አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤ 2 የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ 2 የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው። 18ስለ ዛብሎንም እንዲህ አለ፥ ዛብሎን ሆይ፥ በመውጣትህ፥ 2 ይሳኮር ሆይ በድንኳንህ ውስጥ ደስ ይበላችሁ። 19የተሰወረውን የአሸዋውን መዝገብ፥ 2 የባሕሩንም ባለጠግነት ይጠባሉና 2 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ 2 በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ። 20ስለ ጋድም እንዲህ አለ፥ 2 ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፤ 2 እንደ አንበሳይቱ ዐርፎአል፤ 2 ክንድንና ራስን ይቀጠቅጣል። 21በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና 2 የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፤ 2 ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፤ 2 የእግዚአብሔርንም ጽድቅ፥ 2 ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ። 22ስለ ዳንም እንዲህ አለ፥ 2 ዳን የአንበሳ ደቦል ነው፤ 2 ከባሳን ዘልሎ ይወጣል። 23ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ 2 ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል፥ 2 የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ 2 ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል። 24ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ 2 አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፤ 2 በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። 25ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፤ 2 እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል። 26ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ 2 በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ 2 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። 27መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ 2 የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ 2 ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ 2 አጥፋው ይላል። 28እስራኤልም ተማምኖ፥ 2 የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥ 2 እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፤ 2 ሰማያትም ጠልን ያንጠባጥባሉ። 29እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ 2 በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? 2 እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ 2 የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። 2 ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ 2 አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 33: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ