አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8
8
በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የብንያም ትውልድ
1ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፥ 2አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ። 3ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ አዳር፥ ጌራ፥ አቢሁድ፥ 4አቢሱ፥ ናዕማን፥ ኦሖዋ፥ 5ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም። 6እነዚህም የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ 7ናዕማን፥ አኪያ፥ ጌራ እነርሱም ተማረኩ። ዖዛንና አሒሑድን ወለደ። 8ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ። 9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥ 10ይዑጽን፥ ሻክያንና ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ። 11ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ። 12የኤልፍዓልም ልጆች ዔቤር፥ ሚሻም፥ አኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ፤ 13በሪዓ፥ ሽማዕ፥ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ 14አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥ 15ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥ 16ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች፤ 17ዝባድያ፥ ሜሱላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፥ 18ይሽምራይ፥ ይዝሊያና ዮባብ፥ የኤልፍዓል ልጆች፤ 19ያቂም ዝክሪ፥ ዘብዲ፥ 20ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ 21ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች፤ 22ይሽጳን፥ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ 23ዓብዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፥ 24ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥ 25ይፍዴያና ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች፤ 26ሸምሽራይ፥ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ 27ያሬሽያ፥ ኤልያስና ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች። 28እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
29የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥ 30የበኵር ልጁ ዓብዶን፥ ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥ 31ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር በገባዖን ተቀመጡ። 32ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ።
የንጉሥ ሳኦል ቤተሰብ
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ። 34የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ። 35የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ። 36አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትንና ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ። 37ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁም ረፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤ 38ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሽዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ። 39የወንድሙም የአሴል ልጆች፥ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት። 40የኡላም ልጆች ጽኑዓን፥ ኀያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ