አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 4
4
የይሁዳ ትውልድ
1የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚሆር፥ ሦባል ናቸው። 2የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው። 3እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ። 4የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ የሑሻም አባት ኤጽር፤ እነዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጆች ናቸው። 5ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። 6ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የነዕራ ልጆች ናቸው። 7የሔላም ልጆች ዴሬት፥ ይጽሐር፥ ኤትናን ናቸው። 8ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ። 9ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን “ያቤጽ” ብላ ጠራችው። 10ያቤጽም “እባክህ! መባረክን ባርከኝ፤ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ፤” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
11የሹሐም ወንድም ክሉብ የኤሽቶንን አባት ምሒርን ወለደ። 12ኤሽቶንም ቤትራፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው። 13የቄኔዝም ልጆች ጎቶንያልና ሠራያ ነበሩ። የጎቶንያልም ልጅ ሐታት ነበረ። 14መዖኖታይ ዖፍራን ወለደ። ሠራያም የጌሃራሽምን አባት ኢዮአብን ወለደ፤ እነርሱም ጠራቢዎች ነበሩ። 15የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ። 16የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። የይሃሌልኤል ልጆች ዚፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ። 17የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ። 18አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው። 19የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ። 20የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ። 21የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥ 22ዮቂም፥ የኮዜባ ሰዎች፥ ኢዮአስ፥ ሞዓብን የገዛ ሣራፍ፥ ያሹቢሌሔም ነበሩ። 23ይህ ዝና ከቀድሞ ጀምሮ ነበረ። እነዚህ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። በዚያ በንጉሡ ዘንድ ስለ ሥራው ይቀመጡ ነበር።
የስምዖን ትውልድ
24የስምዖንም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪን፥ ዛራ፥ ሳኡል፤ 25ልጁ ሰሎም፥ ልጁ መብሳም፥ ልጁ ማስማዕ። 26የማስማዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙኤል፥ ልጁ ዘኩር፥ ልጁ ሰሜኢ። 27ለሰሜኢም ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ለወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ወገናቸውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አልተባዙም። 28በቤርሳቤህም፥ በሞላዳ፥ በሐጸርሹዓል፥ 29በቢልሃ፥ በዔጼም፥ በቶላድ፥ 30በቤቱኤል፥ በሔርማ፥ በጺቅላግ፥ 31በቤትማርካቦት፥ በሐጸርሱሲም፥ በቤትቢሪ፥ በሸዓራይም ይቀመጡ ነበር። እስከ ዳዊትም መንግሥት ድረስ ከተሞቻቸው እነዚህ ነበሩ። 32መንደሮቻቸው ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኬን፥ ዓሻን፥ አምስቱ ከተሞች፤ 33እስከ በኣልም ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩ መንደሮቻቸው ሁሉ ነበሩ። መቀመጫቸውና የትውልዳቸው መዝገቦች እነዚህ ናቸው። 34ምሾባብ፥ የምሌክ፥ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያ፥ 35ኢዮኤል፥ የዮሺብያ ልጅ፥ የሠራያ ልጅ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ፥ 36ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል፥ ዩሲምኤል፥ በናያስ፥ 37የሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ፤ 38እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች በዝተው ነበር። 39ለመንጎቻቸው መሰማርያ ይሹ ዘንድ ወደ ጌዶር መግቢያ እስከ ሸለቆው ምሥራቅ ድረስ ሄዱ። 40የለመለመችም እጅግም ያማረች መሰማርያ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ። 41እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ። 42የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ። 43ያመለጡትንም የአማሌቃውያንን ቅሬታ መቱ፤ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጠዋል።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 4: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ