መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 4
4
1ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤
እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤
ከዝምታሽ በቀር ዐይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤
ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚታይ
እንደ ፍየል መንጋ ነው።
2ጥርሶችሽ ከመታጠቢያ ወጥተው እንደ ተሸለቱ
ሁሉም መንታ መንታ እንደ ወለዱ
ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።
3ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥
ቃልሽም ያማረ ነው፤
ከዝምታሽ በቀር ጕንጮችሽ
እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
4አንገትሽ ለሰልፍ ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራ እንደ ዳዊት ግንብ ነው፤
በውስጡም ሺህ የጦር ዕቃና የኀያላን መሣሪያ ሁሉ ተሰቅሎበታል።
5ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥
በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ
እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።
6ቀኑ እስኪነፍስ ጥላውም እስኪያልፍ ድረስ፥
ወደ ከርቤው ተራራ ወደ ዕጣኑም ኰረብታ እሄዳለሁ።
7ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥
ምንም ነውር የለብሽም።
8ሙሽሪት ሆይ፥ ከሊባኖስ ነዪ፤
ከሊባኖስ ነዪ፤
ከሃይማኖት#“ከአማና ራስ” ይላል። ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥
ከአንበሶች ጕድጓድ፥ ከነብሮችም ተራራ ተመልከቺ።
9እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ልቤን ማረክሽው፤
አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ፥ ከአንገትሽም ድሪ በአንዱ፥
ልቤን ማረክሽው።
10እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ጡቶችሽ እንዴት ያማሩ ናቸው?
ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው።
የሽቱሽም መዓዛው ከሽቱ ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው።
11ሙሽሪት ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ የማር ወለላ ይንጠባጠባል፤
ከምላስሽም በታች ማርና ወተት አለ፥
የልብስሽም መዓዛ እንደ ዕጣን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ሊባኖስ ሽታ” ይላል። መዓዛ ነው።
12እኅቴ ሙሽሪት የተቈለፈች ገነት፥
የተዘጋች ገነት፥ የታተመችም ጕድጓድ ናት።
13 # ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቡቃያሽ” ይላል። መንገድሽም ሮማንና የተመረጠ ፍሬ፥
ቆዕ ከናርዶስ ጋር ያለበት ገነት ነው፥
14ናርዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረፋም፥
ከሊባኖስ እንጨቶች ጋር፥
ከርቤና እሬት ከክቡር ሽቱ ሁሉ ጋር።
15አንቺ የገነት ምንጭ፥ የሕይወት ውኃ ጕድጓድ፥
ከሊባኖስም የሚፈስስ ወንዝ ነሽ።
16የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥
የደቡብም ነፋስ ና፤
በገነቴ ላይ ንፈስ፥
ሽቱዬም ይፍሰስ፤
ልጅ ወንድሜ ወደ ገነቱ ይውረድ፥
መልካሙንም ፍሬ ይብላ።
Currently Selected:
መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 4: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ