መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 1
1
1ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር።
2በአፉ አሳሳም ይስመኛል፥
ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ ያማሩ ናቸው።#በዕብ. ከቍ. 2 እስከ 7 መጨረሻ መርዓት ለመርዓዊ ትናገራለች።
3የሽቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥
ስምህ እንደሚፈስስ ሽቱ ነው፤
ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።
4ከወደ ኋላህም ሳቡህ፥ በሽቱህ መዓዛም እንሮጣለን፤
ንጉሡ ወደ እልፍኙ አገባኝ፤
በአንቺ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፤
ከወይን ጠጅ ይልቅ ጡቶችሽን እንወዳለን፤
አንቺንም መውደድ የተገባ ነው።
5እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤
ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።
6ፀሓይ መልኬን አክስሎታልና
ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ፤
የእናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥
የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፤
ነገር ግን የእኔን የወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
7ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፤
በባልንጀሮችህ መንጎች መካከል የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥
ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመሰጋለህ?
8አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥
ያላወቅሽ እንደ ሆነ የመንጎችን ፍለጋ ተከትለሽ ውጪ፥
የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞች ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።
9ወዳጄ ሆይ፥ በፈርዖን ሰረገሎች እንዳለ ፈረሴ መሰልሁሽ።
10ጕንጮችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥
አንገትሽም በዕንቍ ድሪ ያማረ ነው።
11ባለ ብር ጕብጕብ የሆነ የወርቅ ጠልሰም ያድርጉልሽ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እናደርግልሻለን” ይላል።
12ንጉሡ በማዕድ እስከሚቀርብ ድረስ፥
የእኔ ናርዶስ መዓዛውን ሰጠ።
13ውዴ ለእኔ በጡቶች መካከል እንደሚያርፍ
እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።
14ልጅ ወንድሜ ለእኔ በዐይንጋዲ ወይን ቦታ እንዳለ
እንደ አበባ ዕቅፍ ነው።
15ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤
እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤
ዐይኖችሽም እንደ ርግቦች ናቸው።
16ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥
መልከ መልካምም ነህ፤
አልጋችንም ለምለም ነው።
17የቤታችን ሰረገላ የዝግባ ዛፍ ነው፥
የጣሪያችንም ማዋቀሪያ የጥድ ዛፍ ነው።
Currently Selected:
መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 1: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ