መጽሐፈ ሲራክ 5
5
የየዕለት የሕይወት መመሪያ
1ገንዘብህን በከንቱ አትበትን፤
በቃኝም አትበል።
2የሰውነትህን ፈቃድ አትከተል።
3እኔ ኀይለኛ ነኝ፤ ማንስ ይችለኛል አትበል፥
እግዚአብሔር በቀልን ይበቀላልና።
4ኀጢአት ሠርቼ ፍዳ አልተቀበልሁም አትበል፥
እግዚአብሔር ብዙ ዘመን ይታገሣልና።
5ስለ ኀጢአትህ ንስሓ መግባትን አትፍራ።
የእግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ነው
ኀጢአቴንም ይቅር ይለኛል እያልህ በኀጢአት ላይ ኀጢአትን አትጨምር።
6ምሕረትም መቅሠፍትም ከእርሱ ዘንድ ይመጣልና፤
መቅሠፍቱም በኀጢአተኛ ሰው ላይ ይወርዳል።
7ለእግዚአብሔር መገዛትን ቸል አትበል።
ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ፤
ፍዳህ ከመቅሠፍት ጋራ በመጣብህ ጊዜ በመከራ ትጨነቃለህ።
8በመከራህ ጊዜ አንተን ማዳን አይችልምና፤
ለዐመፃ ገንዘብ አትሳሳ።
ራስን ስለ መግዛትና ግልጽ ስለ መሆን
9ለሰው ሁሉ ምሥጢርህን አታውጣ።
የወደድኸውንም ሁሉ አትከተል፤
ምላሱ ሁለት እንደ ሆነ ኀጢአተኛ አትሁን።
10አንተስ በጥበብህ ጸንተህ ኑር፤
ቃልህም አንድ ይሁን።
11ለመስማትም ፈጣን ሁን፤
ቃልን ለመመለስ ግን የዘገየህ ሁን።
12የምትነግረው ካለህ ለባልንጀራህ ንገረው፤
ያለዚያ ግን እጅህን ባፍህ ላይ አድርግ።
13መከበርህና መዋረድህ ከቃልህ የተነሣ ነው፤
የሰውም ውድቀቱ ከአንደበቱ የተነሣ ነው።
14ሐሜተኛ አትሁን፥ በአንደበትህም አውታታ አትሁን፤
የሌባ እፍረቱ ጥቂት ነው።
አንደበቱ ሁለት የሆነ ሰው ግን መከራው ጽኑ ነው።
15በታላቁም በታናሹም ሰው ዘንድ
ቸር ሆነህ ተገለጥ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 5: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ