የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 6:6-14

ወደ ሮሜ ሰዎች 6:6-14 አማ2000

ነገር ግን የኀ​ጢ​አ​ትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ለው አሮ​ጌው ሰው​ነ​ታ​ችን እንደ ሆነ ይህን እና​ው​ቃ​ለን፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ዳግ​መና ለኀ​ጢ​አት እን​ገዛ ዘንድ አን​መ​ለ​ስም። የሞ​ተስ ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጥ​ቶ​አል። ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ት​ንም ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ደ​ም​ን​ኖር እና​ም​ና​ለን። ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ዳግ​መ​ኛም እን​ደ​ማ​ይ​ሞት፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ሞት እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ዛው እና​ው​ቃ​ለን። የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞ​ቱም ኀጢ​አ​ትን ሻራት፤ የተ​ነ​ሣም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተነሣ። እን​ዲሁ እና​ን​ተም ራሳ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት ምው​ታን አድ​ርጉ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ዋን ሁኑ። በዚህ በሚ​ሞት ሰው​ነ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን አታ​ን​ግ​ሡ​አት፤ ለም​ኞ​ቱም እሽ አት​በ​ሉት። ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጉ እንጂ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት የዐ​መፅ የጦር መሣ​ሪያ አታ​ድ​ር​ጉት፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ የጦር መሣ​ሪያ አድ​ርጉ። እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አት አት​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ታ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ገብ​ታ​ች​ኋ​ልና።