መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም። አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም። ሁሉም ተባብሮ በደለ፤ በጎ ሥራንም የሚሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም። ጕረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በአንደበታቸውም ሸነገሉ፤ ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መራራ ነው፤ መርገምንም የተሞላ ነው። እግሮቻቸውም ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው። በመንገዳቸው ጥፋትና ጕስቍልና አለ። የሰላምን መንገድ አያውቋትም። በዐይኖቻቸውም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።” አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን። ከኦሪት የተነሣ ኀጢአት ስለ ታወቀች ሰው ሁሉ የኦሪትን ሥርዐት በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት አይጸድቅም። አሁን ግን በኦሪትና በነቢያት የተመሰከረላት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገለጠች። የሚያምኑበት ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን በእግዚአብሔር ዘንድ ይጸድቃሉ። በዚህም ልዩነት የለም፤ ሁሉም ፈጽመው በድለዋልና፤ እግዚአብሔርን ማክበርንም ትተዋልና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 3 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ሮሜ ሰዎች 3
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos