የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 80

80
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በዋ​ሽ​ንት የአ​ሳፍ መዝ​ሙር።
1በረ​ዳ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥
ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እልል በሉ።
2ዝማ​ሬ​ውን አንሡ ከበ​ሮ​ው​ንም ስጡ፥
ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በገና ከመ​ሰ​ንቆ ጋር፤
3በመ​ባቻ ቀን በታ​ወ​ቀ​ችው በዓ​ላ​ችን ቀን
መለ​ከ​ትን ንፉ፤
4ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐቱ ነውና፥
የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ፍርድ ነውና።
5ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከግ​ብፅ በወጣ ጊዜ” ይላል። ለዮ​ሴፍ ምስ​ክ​ርን አቆመ።
የማ​ያ​ው​ቀ​ውን ቋንቋ ሰማ።#ዕብ. “ያላ​ወ​ቅ​ኋ​ትን ቋንቋ ሰማሁ” ይላል።
6ጀር​ባ​ውን ከመ​ስ​ገ​ጃ​ቸው መለሰ፥
እጆ​ቹም በቅ​ር​ጫት ተገዙ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጫን​ቃ​ው​ንም ከሸ​ክም እጆ​ቹ​ንም በቅ​ር​ጫት ከመ​ገ​ዛት አራ​ቅሁ” ይላል።
7በመ​ከ​ራህ ጊዜ ጠራ​ኸኝ፥ አዳ​ን​ሁ​ህም፥
በተ​ሰ​ወረ ዐው​ሎም መለ​ስ​ሁ​ልህ፥
በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም ፈተ​ን​ሁህ።
8ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነ​ግ​ር​ሃ​ለ​ሁም፤
እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ።
9አን​ተስ ብት​ሰ​ማኝ የድ​ን​ገት አም​ላክ አል​ሆ​ን​ህም፥
ለሌላ አም​ላ​ክም አት​ስ​ገድ።
10ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ
እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና፤
አፍ​ህን አስፋ፥ እሞ​ላ​ዋ​ለ​ሁም።
11ሕዝቤ ግን ቃሌን አል​ሰ​ሙ​ኝም፥
እስ​ራ​ኤ​ልም አላ​ደ​መ​ጡ​ኝም።
12እንደ ሥራ​ቸው ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥
በል​ባ​ቸ​ውም ዐሳብ ሄዱ።
13ሕዝ​ቤስ ቃሌን ሰም​ተ​ውኝ ቢሆን፥
እስ​ራ​ኤ​ልም በመ​ን​ገዴ ሄደው ቢሆን፤
14ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ፈጥኜ ባዋ​ረ​ድ​ኋ​ቸው ነበር፥
በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ውም ላይ እጄን በጣ​ልሁ ነበር፤
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ችስ ዋሽ​ተ​ውት ነበር፥
ዘመ​ና​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሆ​ናል፤
16ከስ​ን​ዴም ስብ አበ​ላ​ቸው፥
ከዓ​ለ​ቱም ማር አጠ​ገ​ባ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ