መዝሙረ ዳዊት 78
78
የአሳፍ መዝሙር።
1አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤
ቤተ መቅደስህንም አረከሱ፥
ኢየሩሳሌምንም እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደረጉአት።
2የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፤
3ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥
የሚቀብራቸውም አጡ።
4ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥
በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና መዘበቻ።
5አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ?
ቅንዐትህም እንደ እሳት ይነድዳል?
6በማያውቁህም አሕዛብ ላይ
ስምህንም በማትጠራ መንግሥት#ዕብ. “በማይጠሩ መንግሥታት” ይላል። ላይ መዓትህን አፍስስ፤
7ያዕቆብን በልተውታልና፥
ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና።
8የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥
አቤቱ፥ ምሕረትህ በቶሎ ያግኘን፥
እጅግ ተቸግረናልና።
9አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ ርዳን፥
ስለ ስምህ ክብር አቤቱ፥ ታደገን፥
ስለ ስምህም ኀጢአታችንን አስተስርይልን።
10አሕዛብ፥ “አምላካቸው ወዴት ነው?” እንዳይሉን፥
የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል
በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይዩ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይወቁ” ይላል።
11የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤
እንደ ክንድህም ታላቅነት የተገደሉትን ሰዎች ልጆች ጠብቃቸው።
12አቤቱ፥ የተገዳደሩህን መገዳደራቸውን፥
ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
13እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማሪያህም በጎች፥
ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤
ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 78: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ