መዝሙረ ዳዊት 75
75
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ አሦራውያን የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥
ስሙም በእስራኤል ታላቅ ሆነ።
2በሀገሩም በሰላም ኖረ፥#ዕብ. “ድንኳኑ በሳሌም ነው” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቦታው በሰላም ነበር” ይላል። ማደሪያውም በጽዮን ነው፤
3በዚያም የቀስትን ኀይል፥
ጋሻን፥ ጦርንና ሰልፍንም ሰበረ፤
በዚያም ቀንዶችን ሰበረ።
4አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።
5ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥
ሕልምን አለሙ፥ ያገኙት ግን የለም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አንቀላፉ በእጃቸው ያገኙት የለም” ይላል።
ሰው ሁሉ ለእጁ ባለጠግነት ነው።
6የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ
ፈረሰኞች ሁሉ አንቀላፉ።
7አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤
ቍጣህን ማን ይቃወማል?
8ፍርድን ከሰማይ ታሰማለህ።
ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥
9ልበ የዋሃንን ሁሉ ያድን ዘንድ፥
እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።
10ሰው በፈቃዱ ያመሰግንሃልና፥
ከሕሊናቸው ትርፍም በዓልህን ያደርጋሉ።
11ለአምላካችን ለአግዚአብሔር ስእለትን ሰጡ፤
በዙሪያውም ያሉ ሁሉ እጅ መንሻን ለሚያስፈራው ያገባሉ።
12የአለቆችን ነፍስ ያወጣል፤
በምድርም ነገሥታት ዘንድ ያስፈራል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 75: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ