አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸን? በማሰማሪያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ለምን ተቈጣህ? አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዠሃትንም የርስትህን በትር፥ በውስጥዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ ዐስብ። ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜ በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ። ጠላቶችህ በበዓልህ መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ። እንደ ላይኛው መንገድ፥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በገጀሞ በሮችዋን ሰበሩ። እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት። መቅደስህንም በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ። አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው አሉ፦ “ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓላት ከምድር እንሻር ምልክቱንም አናውቅም፥ ከእንግዲህ ወዲህ ነቢይ የለም፤ እኛም ከእንግዲህ ወዲህ አናውቅም።” አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህንስ ጠላት ሁልጊዜ ያስቈጣዋል? አቤቱ፥ እጅህን ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ? ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ።
መዝሙረ ዳዊት 73 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 73:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች