በማለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እገለጥልሃለሁም። አንተ በደልን የሚወድድ አምላክ አይደለህምና፤ ክፉዎች ከአንተ ጋር አያድሩም። ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ። ሐሰትን የሚናገሩትን ሁሉ ትጥላቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል። እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት በቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ። አቤቱ፥ በጽድቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላቶቼ መንገዴን በፊትህ አቅና።
መዝሙረ ዳዊት 5 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 5:3-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos