መዝ​ሙረ ዳዊት 44:1-13

መዝ​ሙረ ዳዊት 44:1-13 አማ2000

ልቤ መል​ካም ነገ​ርን ተና​ገረ፥ እኔም ሥራ​ዬን ለን​ጉሥ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አን​ደ​በቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው። ውበቱ ከሰው ልጆች ይልቅ ያም​ራል፤ ሞገስ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችህ ፈሰሰ፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባረ​ከህ። ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ። ስለ ቅን​ነ​ትና ስለ የዋ​ህ​ነት ስለ ጽድ​ቅም አቅና፥ ተከ​ና​ወን፥ ንገ​ሥም፤ ቀኝ​ህም በክ​ብር ይመ​ራ​ሃል። ኀያል ሆይ፥ ፍላ​ጻ​ዎ​ችህ የተ​ሳሉ ናቸው፥ አሕ​ዛብ በበ​ታ​ችህ ይወ​ድ​ቃሉ። በን​ጉሥ ጠላ​ቶች ልብ ውስጥ ይገ​ባሉ፥ አም​ላክ ሆይ፥ ዙፋ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ በትረ መን​ግ​ሥ​ትህ የጽ​ድቅ በትር ነው። ጽድ​ቅን ወደ​ድህ፥ ዐመ​ፃ​ንም ጠላህ፤ ስለ​ዚህ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ችህ ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ የደ​ስታ ዘይ​ትን ቀባህ። ከር​ቤና ሽቱ ዝባ​ድም በል​ብ​ሶ​ችህ ናቸው። የን​ግ​ሥት ሴቶች ልጆች ለክ​ብ​ርህ ናቸው፤ በወ​ርቅ ልብስ ተጐ​ና​ጽ​ፋና ተሸ​ፋ​ፍና ንግ​ሥ​ቲቱ በቀ​ኝህ ትቆ​ማ​ለች። ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮ​ሽ​ንም አዘ​ን​ብዪ፤ ወገ​ን​ሽን ያባ​ት​ሽ​ንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበ​ት​ሽን ወድ​ዶ​አ​ልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና። የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ። ለሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብ​ርዋ ነው፤ በወ​ርቀ ዘቦ ልብስ የተ​ጐ​ና​ጸ​ፈ​ችና የተ​ሸ​ፋ​ፈ​ነች ናት።