መዝ​ሙረ ዳዊት 33:16-21

መዝ​ሙረ ዳዊት 33:16-21 አማ2000

መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን ከም​ድር ያጠፋ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉን በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ ነው። ጻድ​ቃን ጮኹ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ​ቸው፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ አዳ​ና​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል። የጻ​ድ​ቃን መከ​ራ​ቸው ብዙ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሁሉ ያድ​ና​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቃል፥ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አይ​ሰ​በ​ርም። የኃ​ጥእ ሞቱ ክፉ ነው ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ጠሉ ይጸ​ጸ​ታሉ።