መዝሙረ ዳዊት 30
30
ለመዘምራን አለቃ በማድነቅ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለምም አልፈር፤
በጽድቅህም አስጥለኝ፥ አድነኝም።
2ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ፤
ታድነኝ ዘንድ አምላኬ መድኀኒቴና የመጠጊያዬ ቤት ሁነኝ።
3ኀይሌና መጠጊያዬ አንተ ነህና
ስለ ስምህ ምራኝ፥ መግበኝም፤
4አቤቱ፥ አንተ ረዳቴ#ዕብ. “መታመኛዬ” ይላል። ነህና
ከሰወሩብኝ ከዚች ወጥመድ አውጣኝ።
5በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤
የጽድቅ አምላክ እግዚአብሔር፥ ተቤዠኝ።
6ከንቱን ነገር የሚጠብቀውን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ ሊ. በብዙ ቍጥር ነው። ሁሉ ሁልጊዜ ጠላህ፤
እኔ ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።
7በትድግናህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በምሕረትህ” ይላል። ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ።
መከራዬን አይተሃልና፥
ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና።
8በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም፥
በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ።
9ተቸግሬአለሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥
ዐይኔም ከቍጣ የተነሣ ታወከች፥
ነፍሴም፥ ሆዴም።
10ሕይወቴ በመከራ አልቋልና፥
ዘመኔም በጩኸት፤ ኀይሌ በችግር ደከመ፥
አጥንቶቼም ሁሉ ተነዋወጡ።
11በጠላቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰደብሁ፥
ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ፥
ለዘመዶቼም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለሚያውቀኝ” ይላል። አስፈሪ ሆንሁ፤
በሜዳ ያዩኝም ከእኔ ሸሹ።
12እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተረሳሁ” ይላል።
እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።
13በዙሪያዬ የከበቡኝን ድምፅ ሰምቻለሁና፤
በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፥
ነፍሴን ለመንጠቅ በተማከሩ ጊዜ።
14አቤቱ፥ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ፤
አንተ አምላኬ ነህ አልሁ።
15ርስቴ በእጅህ ነው፤
ከጠላቶቼ እጅና ከከበቡኝ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚያሳድዱኝ” ይላል። አድነኝ።
16ፊትህን በባሪያህ ላይ አብራ፥
ስለ ምሕረትህም አድነኝ።
17አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፤
ሸንጋዮች ይፈሩ፥ ወደ ሲኦልም ይውረዱ።
18በትዕቢትና በመናቅ
በጻድቅ ላይ ዐመፃን የሚናገሩ
የሽንገላ ከንፈሮች ወዮላቸው።#ዕብ. እና ግሪክ አባ. ሊ. “ድዳ ይሁኑ” ይላል።
19 # መዝ. 30 ቁ. 19 ከዕብራይስጥ ይለያል። አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ ብዛት
የሚፈሩህን ሰወርኻቸው፥
በሰው ልጆች ፊት የሚታመኑብህንም አዳንኻቸው።
20በፊትህ ጥላ ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ፥
በመጋረጃህም ከአንደበት ሽንገላ ትሸፍናቸዋለህ።
21በመከራዬ ብዛት ጊዜ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በተመሸገ ከተማ” ይላል። ምሕረቱን በእኔ ላይ የገለጠ
እግዚአብሔር ይመስገን።
22እኔስ ከዐይኖችህ ፊት ተጣልሁ ብዬ ነበር።
ስለዚህ ወደ እርሱ የጮኽሁትን
የልመናዬን ቃል ሰማኝ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በቅርብ ነው።
23ጻድቃን ሁላችሁ፥ እግዚአብሔርን ውደዱት፤
እግዚአብሔር ጽድቅን ይሻልና፥
ትዕቢትንም የሚሹትን ፈጽሞ ይበቀላቸዋል።
24በእግዚአብሔር የምታምኑ ሁላችሁ፥
ታገሡ ልባችሁንም አጽኑ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 30: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ