የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 27

27
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ።
ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ።
2በቤተ መቅ​ደ​ስህ እጆ​ችን ባነ​ሣሁ ጊዜ፥
ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን የል​መ​ና​ዬን ቃል ስማ።
3ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ነፍ​ሴን አት​ው​ሰ​ዳት፤
ክፋ​ትም በል​ባ​ቸው እያለ ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ጋር ሰላ​ምን ከሚ​ና​ገሩ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ጋር አት​ጣ​ለኝ።
4እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤
እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤
ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።
5ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ
ወደ እጆ​ቹም ተግ​ባር አላ​ሰ​ቡ​ምና
አፍ​ር​ሳ​ቸው፥ አት​ሥ​ራ​ቸ​ውም።
6የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰም​ቶ​ኛ​ልና
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ቴና መታ​መ​ኛዬ ነው፤
ልቤ በእ​ርሱ ታመነ፥ እር​ሱም ይረ​ዳ​ኛል፤
ሥጋ​ዬም ለመ​ለመ፥ ፈቅ​ጄም አም​ነ​ዋ​ለሁ።#ዕብ. “በመ​ዝ​ሙር አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ” ይላል።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ኀይ​ላ​ቸው ነው፥
ለመ​ሲሑ የመ​ድ​ኀ​ኒቱ መታ​መኛ ነው።
9ሕዝ​ብ​ህን አድን፥ ርስ​ት​ህ​ንም ባርክ፥
ጠብ​ቃ​ቸው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ከፍ ከፍ አድ​ር​ጋ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ