የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 25

25
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ እኔ በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለ​ሁና ፍረ​ድ​ልኝ፤
እን​ዳ​ል​ደ​ክም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመ​ንሁ።
2አቤቱ፥ ፈት​ነኝ መር​ም​ረ​ኝም፤
ኵላ​ሊ​ቴ​ንና ልቤን ፈትን።
3ምሕ​ረ​ትህ በዐ​ይኔ ፊት ነው፥
በማ​ዳ​ን​ህም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእ​ው​ነ​ት​ህም” ይላል። ደስ አለኝ፤
4በከ​ንቱ ሸንጎ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፥
ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር አል​ገ​ባ​ሁም።
5የክ​ፉ​ዎ​ችን ማኅ​በር ጠላሁ፥
ከከ​ዳ​ተ​ኞች ጋር አል​ቀ​መ​ጥም።
6እጆቼን በን​ጽ​ሕና አጥ​ባ​ለሁ፤
አቤቱ፥ መሠ​ዊ​ያ​ህን እዞ​ራ​ለሁ፥
7የም​ስ​ጋ​ና​ህን ቃል እሰማ ዘንድ፥
ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም ሁሉ እነ​ግር ዘንድ።
8አቤቱ፥ የቤ​ት​ህን ጌጥ
የክ​ብ​ር​ህ​ንም ማደ​ሪያ ቦታ ወደ​ድሁ።
9ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ጋር ነፍ​ሴን፥
ከደም ሰዎ​ችም ጋር ሕይ​ወ​ቴን አት​ጣ​ላት።
10በእ​ጃ​ቸው ተን​ኮል አለ​ባ​ቸው፥
ቀኛ​ቸ​ውም መማ​ለ​ጃን ተሞ​ል​ታ​ለች።
11እኔ ግን በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለሁ፤
አቤቱ፦ አድ​ነኝ ይቅ​ርም በለኝ።
12እግ​ሮቼ በቅ​ን​ነት ቆመ​ዋ​ልና፤
አቤቱ፥ በማ​ኅ​በር አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ