የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 151

151
ከቍ​ጥር የወጣ መዝ​ሙር ስለ ራሱ።
1ከወ​ን​ድ​ሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበ​ርሁ፥
በአ​ባ​ቴም ቤት ወጣት ነበ​ርሁ፥
ያባ​ቴ​ንም በጎች እጠ​ብቅ ነበር።
2እጆቼ መሰ​ንቆ ይመቱ ነበር።
ጣቶ​ቼም በገና ይደ​ረ​ድሩ ነበር።
3ለጌ​ታዬ ማን ነገ​ረው?
እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ሰማኝ።
4እርሱ መል​አ​ኩን ልኮ አዳ​ነኝ፥
የአ​ባ​ቴን በጎች ከም​ጠ​ብ​ቅ​በት ወሰ​ደኝ፤
የተ​ቀ​ደሰ ቅባ​ትን ቀባኝ፤
5ወን​ድ​ሞቼ ግን፥ ያማ​ሩና ያደጉ ነበሩ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ነ​ርሱ ደስ አላ​ለ​ውም።
6ልዩ ወገ​ንን#ኢሎ​ፍ​ላ​ዊ​ውን። ልገ​ጥ​መው ወጣሁ።
በረ​ከሱ ጣዖ​ቶ​ቹም ረገ​መኝ።
7እኔም ከወ​ንዝ ሦስት#በ 1ኛ ሳሙ. ምዕ. 17 ቍ. 40 “አም​ስት” ይላል። ድን​ጋ​ዮ​ችን አነ​ሣሁ፥
ግን​ባ​ሩ​ንም በወ​ን​ጭፍ መታ​ሁት።
ያን​ጊ​ዜም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ወደቀ።#ቍ. 7 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
8በላዩ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰይፍ ወሰ​ድሁ፥
የጎ​ል​ያ​ድ​ንም ቸብ​ቸቦ ቈረ​ጥሁ።
ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ስድ​ብን አራ​ቅሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ