የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 147

147
የሐ​ጌና የዘ​ካ​ር​ያስ መዝ​ሙር።
ሃሌ ሉያ።
1ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኚ፥
2ጽዮ​ንም ሆይ፥ አም​ላ​ክ​ሽን አመ​ስ​ግኚ፤
የደ​ጆ​ች​ሽን መወ​ር​ወ​ሪያ አጽ​ን​ቶ​አ​ልና፥
ልጆ​ች​ሽ​ንም በው​ስ​ጥሽ ባር​ኮ​አ​ልና።
3ለወ​ሰ​ኖ​ች​ሽም ሰላ​ምን አደ​ረገ፥
የስ​ን​ዴ​ንም ስብ አጠ​ገ​በሽ።
4ቃሉን ወደ ምድር ይል​ካል፥
ነገ​ሩም እጅግ ፈጥኖ ይሮ​ጣል።
5በረ​ዶ​ውን እንደ ባዘቶ ይሰ​ጣል፤
ጉሙን እንደ አመድ ይበ​ት​ነ​ዋል፤
6በረ​ዶ​ውን እንደ ፍር​ፋሪ ያወ​ር​ዳል፤
ቅዝ​ቃ​ዜ​ው​ንስ ማን ይቋ​ቋ​ማል?
7ቃሉን ልኮ ያቀ​ል​ጠ​ዋል፤
ነፋ​ሱን ያነ​ፍ​ሳል፥ ውኆ​ች​ንም ያፈ​ስ​ሳል።
8ቃሉን ለያ​ዕ​ቆብ፥
ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ይና​ገ​ራል።
9ለሌ​ሎች አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም፥
ፍር​ዱ​ንም አል​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ