የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 142

142
ልጁ ባሳ​ደ​ደው ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥
በእ​ው​ነ​ትህ ልመ​ና​ዬን አድ​ምጥ፥
በጽ​ድ​ቅ​ህም መል​ስ​ልኝ።
2ሕያው ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና
ከባ​ሪ​ያህ ጋር ወደ ክር​ክር አት​ግባ።
3ጠላት ነፍ​ሴን ከብ​ቦ​አ​ታ​ልና
ሕይ​ወ​ቴ​ንም በም​ድር ውስጥ አዋ​ር​ዶ​አ​ታል፥
ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨ​ለማ አኖ​ሩኝ።
4ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥
ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።
5የቀ​ድ​ሞ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፥
ሥራ​ህ​ንም ሁሉ አነ​በ​ብሁ፤
የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ አነ​ብ​ባ​ለሁ።
6እጆ​ቼን ወደ አንተ ዘረ​ጋሁ፤
ነፍ​ሴም እንደ ምድረ በዳ አን​ተን ተጠ​ማች።
7አቤቱ፥ ፈጥ​ነህ ስማኝ፥ ሰው​ነቴ አል​ቃ​ለች፤
ፊት​ህ​ንም ከእኔ አት​መ​ልስ፥
ወደ ጕድ​ጓ​ድም እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ አል​ሁን።
8አቤቱ፥ አን​ተን ታም​ኛ​ለ​ሁና፥
በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን አሰ​ማኝ፤
አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አን​ሥ​ቻ​ለ​ሁና
የም​ሄ​ድ​ባ​ትን መን​ገድ ምራኝ።
9አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማ​ጽ​ኛ​ለ​ሁና
ከጠ​ላ​ቶቼ አድ​ነኝ።
10አቤቱ፥ አንተ አም​ላኬ ነህና ፈቃ​ድ​ህን ለማ​ድ​ረግ አስ​ተ​ም​ረኝ፤
ቅዱስ መን​ፈ​ስ​ህም በጽ​ድቅ ምድር ይም​ራኝ።
11አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድ​ር​ገኝ፤
ስለ ጽድ​ቅ​ህም ነፍ​ሴን ከመ​ከ​ራዋ አው​ጣት።
12በፈ​ቃ​ድህ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በም​ሕ​ረ​ትህ” ይላል። ጠላ​ቶቼን አጥ​ፋ​ቸው፥
እኔ ባሪ​ያህ ነኝና
ነፍ​ሴን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ትን ሁሉ አጥ​ፋ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ